1 ቆሮንቶስ 14:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 ወንድሞች፣ በማስተዋል ችሎታችሁ እንደ ሕፃናት አትሁኑ፤+ ለክፋት ግን ሕፃናት ሁኑ፤+ በማስተዋል ችሎታችሁም የጎለመሳችሁ ሁኑ።+ ዕብራውያን 5:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ጠንካራ ምግብ ግን ትክክልና ስህተት የሆነውን ነገር መለየት እንዲችሉ የማስተዋል ችሎታቸውን በማሠራት ላሠለጠኑ* ጎልማሳ ሰዎች ነው።