ሮም 15:5, 6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ጽናትንና መጽናኛን የሚሰጠው አምላክ፣ ሁላችሁም ክርስቶስ ኢየሱስ የነበረው ዓይነት አስተሳሰብ እንዲኖራችሁ ያድርግ፤ 6 ይኸውም በኅብረትና+ በአንድ ድምፅ* የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክና አባት እንድታከብሩ ነው። 1 ቆሮንቶስ 1:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 እንግዲህ ወንድሞች፣ ሁላችሁም ንግግራችሁ አንድ እንዲሆንና በመካከላችሁ መከፋፈል እንዳይኖር፣+ ከዚህ ይልቅ በአስተሳሰብም ሆነ በዓላማ ፍጹም አንድነት እንዲኖራችሁ+ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አጥብቄ አሳስባችኋለሁ። 2 ቆሮንቶስ 13:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 በተረፈ ወንድሞች፣ መደሰታችሁን፣ መስተካከላችሁን፣ ማጽናኛ መቀበላችሁን፣+ በሐሳብ መስማማታችሁንና+ በሰላም መኖራችሁን ቀጥሉ፤+ የፍቅርና የሰላም አምላክም+ ከእናንተ ጋር ይሆናል። ፊልጵስዩስ 2:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ፍጹም አንድነት ኖሯችሁና* አንድ ዓይነት አስተሳሰብ ይዛችሁ በአንድ ሐሳብና በአንድ ፍቅር በመኖር ደስታዬን የተሟላ አድርጉልኝ።+ 1 ጴጥሮስ 3:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 በመጨረሻም ሁላችሁም የአስተሳሰብ አንድነት* ይኑራችሁ፤+ የሌላውን ስሜት የምትረዱ ሁኑ፤ የወንድማማች መዋደድ ይኑራችሁ፤ ከአንጀት የምትራሩ ሁኑ፤+ ትሑታን ሁኑ።+
5 ጽናትንና መጽናኛን የሚሰጠው አምላክ፣ ሁላችሁም ክርስቶስ ኢየሱስ የነበረው ዓይነት አስተሳሰብ እንዲኖራችሁ ያድርግ፤ 6 ይኸውም በኅብረትና+ በአንድ ድምፅ* የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክና አባት እንድታከብሩ ነው።
10 እንግዲህ ወንድሞች፣ ሁላችሁም ንግግራችሁ አንድ እንዲሆንና በመካከላችሁ መከፋፈል እንዳይኖር፣+ ከዚህ ይልቅ በአስተሳሰብም ሆነ በዓላማ ፍጹም አንድነት እንዲኖራችሁ+ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አጥብቄ አሳስባችኋለሁ።
11 በተረፈ ወንድሞች፣ መደሰታችሁን፣ መስተካከላችሁን፣ ማጽናኛ መቀበላችሁን፣+ በሐሳብ መስማማታችሁንና+ በሰላም መኖራችሁን ቀጥሉ፤+ የፍቅርና የሰላም አምላክም+ ከእናንተ ጋር ይሆናል።
8 በመጨረሻም ሁላችሁም የአስተሳሰብ አንድነት* ይኑራችሁ፤+ የሌላውን ስሜት የምትረዱ ሁኑ፤ የወንድማማች መዋደድ ይኑራችሁ፤ ከአንጀት የምትራሩ ሁኑ፤+ ትሑታን ሁኑ።+