የሐዋርያት ሥራ 16:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 ከዚያም ተነስተን የሮማውያን ቅኝ ግዛትና የመቄዶንያ አውራጃ ቁልፍ ከተማ ወደሆነችው ወደ ፊልጵስዩስ+ መጣን። በዚህች ከተማም ለተወሰኑ ቀናት ቆየን። የሐዋርያት ሥራ 16:22-24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 ሕዝቡም በአንድነት በእነሱ ላይ ተነሳ፤ የከተማዋ ሕግ አስከባሪዎችም ልብሳቸውን ከገፈፏቸው በኋላ በበትር እንዲደበደቡ አዘዙ።+ 23 በጣም ከደበደቧቸው በኋላ እስር ቤት አስገቧቸው፤ የእስር ቤቱንም ጠባቂ በደንብ እንዲጠብቃቸው አዘዙት።+ 24 እሱም እንዲህ ያለ ትእዛዝ ስለተሰጠው ወደ እስር ቤቱ ውስጠኛ ክፍል አስገብቶ እግራቸውን በእግር ግንድ አሰረው።
22 ሕዝቡም በአንድነት በእነሱ ላይ ተነሳ፤ የከተማዋ ሕግ አስከባሪዎችም ልብሳቸውን ከገፈፏቸው በኋላ በበትር እንዲደበደቡ አዘዙ።+ 23 በጣም ከደበደቧቸው በኋላ እስር ቤት አስገቧቸው፤ የእስር ቤቱንም ጠባቂ በደንብ እንዲጠብቃቸው አዘዙት።+ 24 እሱም እንዲህ ያለ ትእዛዝ ስለተሰጠው ወደ እስር ቤቱ ውስጠኛ ክፍል አስገብቶ እግራቸውን በእግር ግንድ አሰረው።