1 ቆሮንቶስ 11:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 እኔ የክርስቶስን አርዓያ እንደምከተል እናንተም የእኔን አርዓያ ተከተሉ።+ ፊልጵስዩስ 3:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ወንድሞች፣ ሁላችሁም የእኔን ምሳሌ ተከተሉ፤+ እንዲሁም እኛ ከተውንላችሁ ምሳሌ ጋር በሚስማማ መንገድ የሚመላለሱትን ሁሉ ልብ ብላችሁ ተመልከቱ። 2 ተሰሎንቄ 3:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ይህን ያደረግነው የእኛን አርዓያ እንድትከተሉ+ ራሳችንን ለእናንተ ምሳሌ አድርገን ለማቅረብ ብለን እንጂ ሥልጣን ሳይኖረን ቀርቶ አይደለም።+