14 እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ቀበቶ ታጥቃችሁና+ የጽድቅን ጥሩር ለብሳችሁ+ ጸንታችሁ ቁሙ፤ 15 እንዲሁም የሰላምን ምሥራች ለማወጅ ዝግጁ በመሆን እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ።+ 16 ከዚህ ሁሉ በተጨማሪ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ማምከን የምትችሉበትን ትልቅ የእምነት ጋሻ አንሱ።+ 17 በተጨማሪም የመዳንን የራስ ቁር አድርጉ፤+ እንዲሁም የመንፈስን ሰይፍ ይኸውም የአምላክን ቃል ያዙ፤+