1 ጢሞቴዎስ 4:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ለራስህና ለምታስተምረው ትምህርት ምንጊዜም ትኩረት ስጥ።+ በእነዚህ ነገሮች ጽና፤ ይህን በማድረግ ራስህንም ሆነ የሚሰሙህን ታድናለህና።+ 2 ጢሞቴዎስ 1:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ከእኔ የሰማኸውን የትክክለኛ* ትምህርት+ መሥፈርት* ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር ባለህ አንድነት ካገኘኸው እምነትና ፍቅር ጋር አጥብቀህ ያዝ።