ዮሐንስ 3:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እውነት እውነት እልሃለሁ፣ ሰው ከውኃና+ ከመንፈስ+ ካልተወለደ በቀር ወደ አምላክ መንግሥት ሊገባ አይችልም። ሮም 8:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 ይህም ብቻ ሳይሆን የውርሻችንን በኩራት ይኸውም መንፈስን ያገኘን እኛ ራሳችንም በቤዛው አማካኝነት ከሥጋዊ አካላችን ነፃ በመውጣት አምላክ ልጆቹ አድርጎ እንዲወስደን+ በጉጉት እየተጠባበቅን በውስጣችን እንቃትታለን።+ 2 ቆሮንቶስ 5:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 በመሆኑም ማንም ከክርስቶስ ጋር አንድነት ካለው አዲስ ፍጥረት ነው፤+ አሮጌዎቹ ነገሮች አልፈዋል፤ እነሆ፣ አዳዲስ ነገሮች ወደ ሕልውና መጥተዋል!
23 ይህም ብቻ ሳይሆን የውርሻችንን በኩራት ይኸውም መንፈስን ያገኘን እኛ ራሳችንም በቤዛው አማካኝነት ከሥጋዊ አካላችን ነፃ በመውጣት አምላክ ልጆቹ አድርጎ እንዲወስደን+ በጉጉት እየተጠባበቅን በውስጣችን እንቃትታለን።+