የሐዋርያት ሥራ 13:38, 39 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 38 “ስለዚህ ወንድሞች፣ በእሱ በኩል የሚገኘው የኃጢአት ይቅርታ አሁን እየታወጀላችሁ እንዳለ እወቁ፤+ 39 በኢየሱስ የሚያምን ማንኛውም ሰው፣ በእሱ አማካኝነት ‘ከበደል ነፃ ነህ’ ሊባል ይችላል፤+ የሙሴ ሕግ ግን እናንተን ከበደል ነፃ ሊያደርጋችሁ አልቻለም።+ ገላትያ 2:15, 16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 በትውልዳችን አይሁዳውያን እንጂ ከአሕዛብ ወገን እንደሆኑት ኃጢአተኞች ያልሆንነው እኛ፣ 16 አንድ ሰው የሚጸድቀው ሕግን በመጠበቅ ሳይሆን በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን+ ብቻ እንደሆነ እንገነዘባለን።+ ስለዚህ ሕግን በመጠበቅ ሳይሆን በክርስቶስ በማመን እንድንጸድቅ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል፤ ምክንያቱም ሕግን በመጠበቅ መጽደቅ የሚችል ሰው* የለም።+ ዕብራውያን 10:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ሕጉ ወደፊት ለሚመጡት መልካም ነገሮች ጥላ+ ነው እንጂ የእነዚህ ነገሮች እውነተኛ አካል አይደለም፤ ስለዚህ ሕጉ ከዓመት ዓመት እነዚያኑ መሥዋዕቶች በማቅረብ አምላክን የሚያመልኩትን ሰዎች ፍጹም ሊያደርጋቸው አይችልም።*+
38 “ስለዚህ ወንድሞች፣ በእሱ በኩል የሚገኘው የኃጢአት ይቅርታ አሁን እየታወጀላችሁ እንዳለ እወቁ፤+ 39 በኢየሱስ የሚያምን ማንኛውም ሰው፣ በእሱ አማካኝነት ‘ከበደል ነፃ ነህ’ ሊባል ይችላል፤+ የሙሴ ሕግ ግን እናንተን ከበደል ነፃ ሊያደርጋችሁ አልቻለም።+
15 በትውልዳችን አይሁዳውያን እንጂ ከአሕዛብ ወገን እንደሆኑት ኃጢአተኞች ያልሆንነው እኛ፣ 16 አንድ ሰው የሚጸድቀው ሕግን በመጠበቅ ሳይሆን በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን+ ብቻ እንደሆነ እንገነዘባለን።+ ስለዚህ ሕግን በመጠበቅ ሳይሆን በክርስቶስ በማመን እንድንጸድቅ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል፤ ምክንያቱም ሕግን በመጠበቅ መጽደቅ የሚችል ሰው* የለም።+
10 ሕጉ ወደፊት ለሚመጡት መልካም ነገሮች ጥላ+ ነው እንጂ የእነዚህ ነገሮች እውነተኛ አካል አይደለም፤ ስለዚህ ሕጉ ከዓመት ዓመት እነዚያኑ መሥዋዕቶች በማቅረብ አምላክን የሚያመልኩትን ሰዎች ፍጹም ሊያደርጋቸው አይችልም።*+