37 “‘ለይሖዋ በእሳት የሚቀርበውን መባ ማለትም የሚቃጠለውን መባ፣+ ከመሥዋዕቱ ጋር የሚቀርበውን የእህል መባና+ በየዕለቱ እንዲቀርቡ የተመደቡትን የመጠጥ መባዎች+ ለማቅረብ ቅዱስ ጉባኤዎች+ እንደሆኑ አድርጋችሁ የምታውጇቸው በየወቅቱ የሚከበሩት የይሖዋ በዓላት+ እነዚህ ናቸው። 38 እነዚህ ለይሖዋ ልትሰጧቸው ከሚገቡት በይሖዋ ሰንበቶች+ ላይ ከሚቀርቡት፣ ከስጦታዎቻችሁ፣+ ስእለት ለመፈጸም ከምታቀርቧቸው መባዎችና+ ከፈቃደኝነት መባዎቻችሁ+ በተጨማሪ የምታቀርቧቸው ናቸው።