6 ሙሴም ከደሙ ግማሹን ወስዶ በሳህኖች ውስጥ አስቀመጠው፤ ግማሹን ደም ደግሞ በመሠዊያው ላይ ረጨው። 7 ከዚያም የቃል ኪዳኑን መጽሐፍ ወስዶ ድምፁን ከፍ በማድረግ ለሕዝቡ አነበበ።+ ሕዝቡም “ይሖዋ የተናገረውን ሁሉ ለመፈጸምና ለመታዘዝ ፈቃደኞች ነን” አሉ።+ 8 በመሆኑም ሙሴ ደሙን ወስዶ በሕዝቡ ላይ ረጨው፤+ እንዲህም አለ፦ “በእነዚህ ቃላት መሠረት ይሖዋ ከእናንተ ጋር የገባው ቃል ኪዳን ደም ይህ ነው።”+