-
ዘፍጥረት 27:27-29አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
27 ስለዚህ ወደ እሱ ቀረበና ሳመው፤ ይስሐቅም የልጁን ልብስ ጠረን አሸተተ።+ ከዚያም ባረከው፤ እንዲህም አለው፦
“አቤት፣ የልጄ ጠረን ይሖዋ እንደባረከው መስክ መዓዛ ነው። 28 እውነተኛው አምላክ የሰማያትን ጠል፣+ የምድርን ለም አፈር+ እንዲሁም የተትረፈረፈ እህልና አዲስ የወይን ጠጅ ይስጥህ።+ 29 ሕዝቦች ያገልግሉህ፤ ብሔራትም ይስገዱልህ። የወንድሞችህ ጌታ ሁን፤ የእናትህም ወንዶች ልጆች ይስገዱልህ።+ የሚረግሙህ ሁሉ የተረገሙ ይሁኑ፤ የሚባርኩህም ሁሉ የተባረኩ ይሁኑ።”+
-