34 ዳዊትም ሳኦልን እንዲህ አለው፦ “አገልጋይህ የአባቱን መንጋ በሚጠብቅበት ጊዜ አንበሳ+ እንዲሁም ድብ ይመጣና ከመንጋው መካከል አንድ በግ ነጥቆ ይወስድ ነበር። 35 እኔም ተከትዬው በመሄድ እመታውና በጉን ከአፉ አስጥለው ነበር። ሊያጠቃኝ በተነሳ ጊዜም ጉሮሮውን አንቄ በመምታት እገድለው ነበር። 36 አገልጋይህ አንበሳውንም ሆነ ድቡን ገድሏል፤ ይህ ያልተገረዘ ፍልስጤማዊም ሕያው በሆነው አምላክ ሠራዊት ላይ ስለተሳለቀ መጨረሻው ከእነሱ እንደ አንዱ ይሆናል።”+