-
ዳንኤል 3:23-25አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
23 ይሁንና ሦስቱ ሰዎች ይኸውም ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብደናጎ እንደታሰሩ በሚንበለበለው የእቶን እሳት ውስጥ ወደቁ።
24 ከዚያም ንጉሥ ናቡከደነጾር በድንጋጤ ከተቀመጠበት ዘሎ ተነሳ፤ ከፍተኛ ባለሥልጣናቱንም “አስረን እሳት ውስጥ የጣልናቸው ሦስት ሰዎች አልነበሩም እንዴ?” ሲል ጠየቃቸው፤ እነሱም “አዎ፣ ንጉሥ ሆይ” ብለው መለሱ። 25 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “እነሆ፣ ያልታሰሩ አራት ሰዎች በእሳቱ መካከል ሲመላለሱ አያለሁ፤ ጉዳትም አልደረሰባቸውም፤ አራተኛውም የአማልክትን ልጅ ይመስላል።”
-