2 በመላእክት አማካኝነት የተነገረው ቃል+ የጸና መሆኑ ከተረጋገጠ እንዲሁም ማንኛውም አለመታዘዝና መተላለፍ ከፍትሕ ጋር የሚስማማ ቅጣት የሚያስከትል ከሆነ+ 3 እንዲህ ያለውን ታላቅ መዳን ቸል ብንል እንዴት ከቅጣት ልናመልጥ እንችላለን?+ ይህ መዳን መጀመሪያ ጌታችን የተናገረው+ ሲሆን እሱን የሰሙት ሰዎችም ለእኛ አረጋግጠውልናል፤ 4 አምላክም በምልክቶች፣ በድንቅ ነገሮች፣ በተለያዩ ተአምራትና+ ከፈቃዱ ጋር በሚስማማ ሁኔታ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን በማደል መሥክሯል።+