ሮም 15:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ክርስቶስ እንኳ ራሱን አላስደሰተምና፤+ ይህም “ሰዎች አንተን ይነቅፉበት የነበረው ነቀፋ በእኔ ላይ ደረሰ” ተብሎ እንደተጻፈው ነው።+ 2 ቆሮንቶስ 12:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ስለሆነም ስለ ክርስቶስ ስል በድክመት፣ በስድብ፣ በእጦት፣ በስደትና በችግር ደስ እሰኛለሁ። ስደክም ያን ጊዜ ብርቱ ነኝና።+ 1 ጴጥሮስ 4:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ለክርስቶስ ስም ስትሉ ብትነቀፉ* ደስተኞች ናችሁ፤+ ምክንያቱም የክብር መንፈስ ይኸውም የአምላክ መንፈስ በእናንተ ላይ ያርፋል።