7 እሱ አምላካችን ነውና፤
እኛ ደግሞ በመስኩ የተሰማራን ሕዝቦች፣
በእሱ እንክብካቤ ሥር ያለን በጎች ነን።+
ዛሬ ድምፁን የምትሰሙ ከሆነ፣+
8 አባቶቻችሁ በምድረ በዳ ሳሉ በመሪባ፣
በማሳህ ቀን እንዳደረጉት ልባችሁን አታደንድኑ፤+
9 በዚያን ጊዜ እነሱ ፈተኑኝ፤+
ሥራዬን ቢያዩም ተገዳደሩኝ።+
10 ያን ትውልድ ለ40 ዓመት ተጸየፍኩት፤
እኔም “ይህ ሕዝብ ሁልጊዜ ልቡ ይስታል፤
መንገዴን ሊያውቅ አልቻለም” አልኩ።
11 በመሆኑም “ወደ እረፍቴ አይገቡም” ብዬ
በቁጣዬ ማልኩ።+