መዝሙር 7:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 እባክህ፣ የክፉ ሰዎች ክፋት እንዲያከትም አድርግ። ጻድቁን ሰው ግን አጽና፤+ልብንና+ ጥልቅ ስሜትን የምትመረምር*+ ጻድቅ አምላክ ነህና።+ መዝሙር 90:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 በደላችንን በፊትህ ታኖራለህ፤*+የደበቅናቸው ነገሮች በፊትህ ብርሃን ተጋልጠዋል።+ ምሳሌ 15:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 መቃብርና* የጥፋት ቦታ* በይሖዋ ፊት ወለል ብለው ይታያሉ።+ የሰዎች ልብማ በፊቱ ምንኛ የተገለጠ ነው!+