መዝሙር 39:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 በእርግጥም ሰው ሁሉ የሚመላለሰው እንደ ጥላ ነው። ላይ ታች የሚለው* በከንቱ ነው። ማን እንደሚጠቀምበት ሳያውቅ ንብረት ያከማቻል።+ ምሳሌ 27:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 ነገ በሚሆነው ነገር አትመካ፤ቀን የሚያመጣውን* አታውቅምና።+ መክብብ 6:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 ሰው በሕይወት ሳለ ይኸውም ከንቱ በሆነውና እንደ ጥላ በሚያልፈው አጭር የሕይወት ዘመኑ ሊያደርገው የሚችለው የተሻለ ነገር ምን እንደሆነ የሚያውቅ ማን ነው?+ እሱ ካለፈስ በኋላ ከፀሐይ በታች የሚሆነውን ነገር ማን ሊነግረው ይችላል?
12 ሰው በሕይወት ሳለ ይኸውም ከንቱ በሆነውና እንደ ጥላ በሚያልፈው አጭር የሕይወት ዘመኑ ሊያደርገው የሚችለው የተሻለ ነገር ምን እንደሆነ የሚያውቅ ማን ነው?+ እሱ ካለፈስ በኋላ ከፀሐይ በታች የሚሆነውን ነገር ማን ሊነግረው ይችላል?