ዘዳግም 14:29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 አምላክህ ይሖዋ የእጅህን ሥራ ሁሉ እንዲባርክልህ+ ከአንተ ጋር ድርሻም ሆነ ውርሻ ያልተሰጠው ሌዋዊ እንዲሁም በከተሞችህ ውስጥ የሚኖሩት የባዕድ አገር ሰዎች፣ አባት የሌላቸው* ልጆችና መበለቶች መጥተው እስኪጠግቡ ድረስ ይብሉ።+ ዘዳግም 27:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 “‘የባዕድ አገሩን ሰው፣ አባት የሌለውን* ልጅ ወይም የመበለቲቱን ፍርድ የሚያዛባ+ የተረገመ ይሁን።’+ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።) መዝሙር 68:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 በተቀደሰ መኖሪያው ያለው አምላክ+አባት ለሌላቸው ልጆች አባት፣ ለመበለቶች ደግሞ ጠባቂ* ነው።+
29 አምላክህ ይሖዋ የእጅህን ሥራ ሁሉ እንዲባርክልህ+ ከአንተ ጋር ድርሻም ሆነ ውርሻ ያልተሰጠው ሌዋዊ እንዲሁም በከተሞችህ ውስጥ የሚኖሩት የባዕድ አገር ሰዎች፣ አባት የሌላቸው* ልጆችና መበለቶች መጥተው እስኪጠግቡ ድረስ ይብሉ።+