ኢሳይያስ 53:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ሰዎች የናቁትና ያገለሉት፣+ሥቃይን ያየ፣* ሕመምንም የሚያውቅ ሰው ነበር። ፊቱ የተሰወረብን ያህል ነበር።* ሰዎች ናቁት፤ እኛም ከቁብ አልቆጠርነውም።+ ዮሐንስ 19:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 እነሱ ግን “አስወግደው! አስወግደው! ስቀለው!”* እያሉ ጮኹ። ጲላጦስም “ንጉሣችሁን ልግደለው?” አላቸው። የካህናት አለቆቹም “ከቄሳር በቀር ሌላ ንጉሥ የለንም” ሲሉ መለሱ።
15 እነሱ ግን “አስወግደው! አስወግደው! ስቀለው!”* እያሉ ጮኹ። ጲላጦስም “ንጉሣችሁን ልግደለው?” አላቸው። የካህናት አለቆቹም “ከቄሳር በቀር ሌላ ንጉሥ የለንም” ሲሉ መለሱ።