መዝሙር 34:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 የይሖዋ ዓይኖች ጻድቃንን ይመለከታሉ፤+ጆሮዎቹም እርዳታ ለማግኘት የሚያሰሙትን ጩኸት ይሰማሉ።+ ማቴዎስ 7:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 የሚለምን ሁሉ ይሰጠዋልና፤+ የሚፈልግ ሁሉ ያገኛል፤ ለሚያንኳኳም ሁሉ ይከፈትለታል። 1 ጴጥሮስ 3:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 የይሖዋ* ዓይኖች ጻድቃንን ይመለከታሉና፤ ጆሮዎቹም ምልጃቸውን ይሰማሉ፤+ የይሖዋ* ፊት ግን ክፉ ነገሮችን በሚያደርጉ ላይ ነው።”+