ዮሐንስ 1:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ቃልም ሥጋ ሆነ፤+ በመካከላችንም ኖረ፤ አንድያ ልጅ+ ከአባቱ እንደሚያገኘው ክብር ያለ ክብሩን አየን፤ እሱም መለኮታዊ ሞገስንና* እውነትን ተሞልቶ ነበር። 1 ቆሮንቶስ 12:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ስለዚህ ይህን እንድታውቁ እወዳለሁ፦ በአምላክ መንፈስ ተመርቶ “ኢየሱስ የተረገመ ነው!” የሚል ማንም የለም፤ እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ ካልሆነ በቀር ማንም “ኢየሱስ ጌታ ነው!” ብሎ ሊናገር አይችልም።+ ራእይ 19:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 እኔም በዚህ ጊዜ ልሰግድለት በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እሱ ግን “ተጠንቀቅ! ፈጽሞ እንዳታደርገው!+ እኔ ከአንተም ሆነ ስለ ኢየሱስ የመመሥከር ሥራ ካላቸው ወንድሞችህ ጋር አብሬ የማገለግል ባሪያ ነኝ።+ ለአምላክ ስገድ!+ ትንቢት የሚነገረው ስለ ኢየሱስ ለመመሥከር ነውና” አለኝ።+
3 ስለዚህ ይህን እንድታውቁ እወዳለሁ፦ በአምላክ መንፈስ ተመርቶ “ኢየሱስ የተረገመ ነው!” የሚል ማንም የለም፤ እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ ካልሆነ በቀር ማንም “ኢየሱስ ጌታ ነው!” ብሎ ሊናገር አይችልም።+
10 እኔም በዚህ ጊዜ ልሰግድለት በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እሱ ግን “ተጠንቀቅ! ፈጽሞ እንዳታደርገው!+ እኔ ከአንተም ሆነ ስለ ኢየሱስ የመመሥከር ሥራ ካላቸው ወንድሞችህ ጋር አብሬ የማገለግል ባሪያ ነኝ።+ ለአምላክ ስገድ!+ ትንቢት የሚነገረው ስለ ኢየሱስ ለመመሥከር ነውና” አለኝ።+