ራእይ 13:16-18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ሰዎች ሁሉ ማለትም ታናናሾችና ታላላቆች፣ ሀብታሞችና ድሆች እንዲሁም ነፃ ሰዎችና ባሪያዎች በቀኝ እጃቸው ወይም በግንባራቸው ላይ ምልክት እንዲደረግባቸው አስገደደ፤+ 17 ይህም የሆነው ምልክቱ ይኸውም የአውሬው ስም+ ወይም የስሙ ቁጥር+ ካለው ሰው በስተቀር ማንም መግዛት ወይም መሸጥ እንዳይችል ነው። 18 ጥበብ የሚያስፈልገው እዚህ ላይ ነው፦ የማስተዋል ችሎታ ያለው ሰው የአውሬውን ቁጥር ያስላ፤ ቁጥሩ የሰው ቁጥር ነውና፤ ቁጥሩም 666 ነው።+ ራእይ 16:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 የመጀመሪያው መልአክ ሄዶ በሳህኑ ውስጥ ያለውን በምድር ላይ አፈሰሰው።+ በዚህ ጊዜም የአውሬው ምልክት በነበራቸውና+ ምስሉን ያመልኩ በነበሩት ሰዎች+ ላይ ጉዳት የሚያስከትልና አስከፊ የሆነ ቁስል+ ወጣባቸው። ራእይ 20:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ዙፋኖችንም አየሁ፤ በዙፋኖቹም ላይ ለተቀመጡት የመፍረድ ሥልጣን ተሰጣቸው። ስለ ኢየሱስ በመመሥከራቸውና ስለ አምላክ በመናገራቸው የተነሳ የተገደሉትን* ሰዎች ነፍሳት* እንዲሁም አውሬውን ወይም ምስሉን ያላመለኩትንና ምልክቱን በግንባራቸውም ሆነ በእጃቸው ላይ ያልተቀበሉትን ሰዎች አየሁ።+ እነሱም ሕያው ሆነው ከክርስቶስ ጋር ለ1,000 ዓመት ነገሡ።+
16 ሰዎች ሁሉ ማለትም ታናናሾችና ታላላቆች፣ ሀብታሞችና ድሆች እንዲሁም ነፃ ሰዎችና ባሪያዎች በቀኝ እጃቸው ወይም በግንባራቸው ላይ ምልክት እንዲደረግባቸው አስገደደ፤+ 17 ይህም የሆነው ምልክቱ ይኸውም የአውሬው ስም+ ወይም የስሙ ቁጥር+ ካለው ሰው በስተቀር ማንም መግዛት ወይም መሸጥ እንዳይችል ነው። 18 ጥበብ የሚያስፈልገው እዚህ ላይ ነው፦ የማስተዋል ችሎታ ያለው ሰው የአውሬውን ቁጥር ያስላ፤ ቁጥሩ የሰው ቁጥር ነውና፤ ቁጥሩም 666 ነው።+
2 የመጀመሪያው መልአክ ሄዶ በሳህኑ ውስጥ ያለውን በምድር ላይ አፈሰሰው።+ በዚህ ጊዜም የአውሬው ምልክት በነበራቸውና+ ምስሉን ያመልኩ በነበሩት ሰዎች+ ላይ ጉዳት የሚያስከትልና አስከፊ የሆነ ቁስል+ ወጣባቸው።
4 ዙፋኖችንም አየሁ፤ በዙፋኖቹም ላይ ለተቀመጡት የመፍረድ ሥልጣን ተሰጣቸው። ስለ ኢየሱስ በመመሥከራቸውና ስለ አምላክ በመናገራቸው የተነሳ የተገደሉትን* ሰዎች ነፍሳት* እንዲሁም አውሬውን ወይም ምስሉን ያላመለኩትንና ምልክቱን በግንባራቸውም ሆነ በእጃቸው ላይ ያልተቀበሉትን ሰዎች አየሁ።+ እነሱም ሕያው ሆነው ከክርስቶስ ጋር ለ1,000 ዓመት ነገሡ።+