ዘፀአት 40:34, 35 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 34 ደመናውም የመገናኛ ድንኳኑን ሸፈነው፤ የይሖዋም ክብር የማደሪያ ድንኳኑን ሞላው።+ 35 ደመናው በመገናኛ ድንኳኑ ላይ አርፎ ስለነበርና የይሖዋም ክብር የማደሪያ ድንኳኑን ስለሞላው ሙሴ ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግባት አልቻለም ነበር።+ 1 ነገሥት 8:10, 11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ካህናቱ ከቅዱሱ ስፍራ በወጡ ጊዜ ደመናው+ የይሖዋን ቤት ሞላው።+ 11 የይሖዋ ክብር የይሖዋን ቤት ሞልቶት ስለነበር ካህናቱ ከደመናው የተነሳ በዚያ ቆመው ማገልገል አልቻሉም።+ ኢሳይያስ 6:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ከድምፁ ጩኸት* የተነሳ የበሩ መቃኖች ተናወጡ፤ ቤቱም በጭስ ተሞላ።+ ሕዝቅኤል 44:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ከዚያም በስተ ሰሜን በሚገኘው በር በኩል ከቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ወዳለው ቦታ አመጣኝ። እኔም ባየሁ ጊዜ የይሖዋ ክብር፣ የይሖዋን ቤተ መቅደስ ሞልቶት ተመለከትኩ።+ በዚህ ጊዜ በግንባሬ መሬት ላይ ተደፋሁ።+
34 ደመናውም የመገናኛ ድንኳኑን ሸፈነው፤ የይሖዋም ክብር የማደሪያ ድንኳኑን ሞላው።+ 35 ደመናው በመገናኛ ድንኳኑ ላይ አርፎ ስለነበርና የይሖዋም ክብር የማደሪያ ድንኳኑን ስለሞላው ሙሴ ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግባት አልቻለም ነበር።+
10 ካህናቱ ከቅዱሱ ስፍራ በወጡ ጊዜ ደመናው+ የይሖዋን ቤት ሞላው።+ 11 የይሖዋ ክብር የይሖዋን ቤት ሞልቶት ስለነበር ካህናቱ ከደመናው የተነሳ በዚያ ቆመው ማገልገል አልቻሉም።+
4 ከዚያም በስተ ሰሜን በሚገኘው በር በኩል ከቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ወዳለው ቦታ አመጣኝ። እኔም ባየሁ ጊዜ የይሖዋ ክብር፣ የይሖዋን ቤተ መቅደስ ሞልቶት ተመለከትኩ።+ በዚህ ጊዜ በግንባሬ መሬት ላይ ተደፋሁ።+