7 አንቺም “ሁልጊዜ ብሎም ለዘላለም እመቤት እሆናለሁ” አልሽ።+
እነዚህን ነገሮች ልብ አላልሽም፤
ነገሩ ምን ፍጻሜ እንደሚኖረው አላሰብሽም።
8 በመሆኑም አንቺ ለሥጋዊ ደስታ ያደርሽ፣+
ተማምነሽ የተቀመጥሽና
በልብሽ “እኔ ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ የለም።+
መበለት አልሆንም።
በምንም ዓይነት የወላድ መሃን አልሆንም” የምትዪ ሴት ሆይ፣+ ይህን ስሚ።
9 ሆኖም እነዚህ ሁለት ነገሮች ይኸውም
የወላድ መሃንነትና መበለትነት በአንድ ቀን በድንገት ይደርሱብሻል።+
በመተት ስለተሞላሽና ታላቅ ኃይል ባለው ድግምት ስለተዘፈቅሽ+
እነዚህ ነገሮች ሁሉ በአንቺ ላይ ይደርሳሉ።+