2 ቆሮንቶስ 6:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ከዚህ ይልቅ በሁሉም ነገር ራሳችንን ብቁ የአምላክ አገልጋዮች አድርገን እናቀርባለን፤+ ይህን የምናደርገው በብዙ ነገር በመጽናት፣ በመከራ፣ በእጦት፣ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች፣+ 2 ቆሮንቶስ 6:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ሐዘንተኞች ተደርገን ብንታይም ምንጊዜም ደስተኞች ነን፤ እንደ ድሆች ብንቆጠርም ብዙዎችን ባለጸጋ እያደረግን ነው፤ ምንም የሌለን ብንመስልም ሁሉ ነገር አለን።+ 1 ጢሞቴዎስ 6:18, 19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 በተጨማሪም መልካም ነገር እንዲያደርጉ፣ በመልካም ሥራዎች ባለጸጋ እንዲሆኑ እንዲሁም ለጋሶችና ለሌሎች ለማካፈል ዝግጁ እንዲሆኑ ምከራቸው፤+ 19 እውነተኛ የሆነውን ሕይወት አጥብቀው መያዝ ይችሉ ዘንድ+ ለራሳቸው ውድ ሀብት ማከማቸታቸውን ይኸውም ለወደፊቱ ጊዜ የሚሆን መልካም መሠረት መጣላቸውን ይቀጥሉ።+ ያዕቆብ 2:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ስሙ። አምላክ በእምነት ባለጸጋ እንዲሆኑና+ እሱን ለሚወዱ ቃል የገባውን መንግሥት እንዲወርሱ ከዓለም አመለካከት አንጻር ድሆች የሆኑትን አልመረጠም?+
4 ከዚህ ይልቅ በሁሉም ነገር ራሳችንን ብቁ የአምላክ አገልጋዮች አድርገን እናቀርባለን፤+ ይህን የምናደርገው በብዙ ነገር በመጽናት፣ በመከራ፣ በእጦት፣ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች፣+
10 ሐዘንተኞች ተደርገን ብንታይም ምንጊዜም ደስተኞች ነን፤ እንደ ድሆች ብንቆጠርም ብዙዎችን ባለጸጋ እያደረግን ነው፤ ምንም የሌለን ብንመስልም ሁሉ ነገር አለን።+
18 በተጨማሪም መልካም ነገር እንዲያደርጉ፣ በመልካም ሥራዎች ባለጸጋ እንዲሆኑ እንዲሁም ለጋሶችና ለሌሎች ለማካፈል ዝግጁ እንዲሆኑ ምከራቸው፤+ 19 እውነተኛ የሆነውን ሕይወት አጥብቀው መያዝ ይችሉ ዘንድ+ ለራሳቸው ውድ ሀብት ማከማቸታቸውን ይኸውም ለወደፊቱ ጊዜ የሚሆን መልካም መሠረት መጣላቸውን ይቀጥሉ።+
5 የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ስሙ። አምላክ በእምነት ባለጸጋ እንዲሆኑና+ እሱን ለሚወዱ ቃል የገባውን መንግሥት እንዲወርሱ ከዓለም አመለካከት አንጻር ድሆች የሆኑትን አልመረጠም?+