መዝሙር 2:8, 9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ጠይቀኝ፤ ብሔራትን ርስትህ፣የምድርንም ዳርቻዎች ግዛትህ አድርጌ እሰጥሃለሁ።+ 9 በብረት በትረ መንግሥት ትሰብራቸዋለህ፤+እንደ ሸክላ ዕቃም ታደቃቸዋለህ።”+ ማቴዎስ 19:28 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “እውነት እላችኋለሁ፣ ሁሉም ነገር አዲስ በሚሆንበት ጊዜ* የሰው ልጅ፣ ክብራማ በሆነው ዙፋኑ ላይ ሲቀመጥ እኔን የተከተላችሁኝ እናንተ በ12 ዙፋኖች ላይ ተቀምጣችሁ በ12ቱ የእስራኤል ነገዶች ላይ ትፈርዳላችሁ።+ ሉቃስ 22:28-30 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 “ይሁን እንጂ እናንተ በፈተናዎቼ+ ከጎኔ ሳትለዩ ቆይታችኋል፤+ 29 አባቴ ከእኔ ጋር ቃል ኪዳን እንዳደረገ ሁሉ እኔም ከእናንተ ጋር ለመንግሥት ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤+ 30 ይኸውም በመንግሥቴ ከማዕዴ እንድትበሉና እንድትጠጡ+ እንዲሁም በዙፋን ተቀምጣችሁ+ በ12ቱ የእስራኤል ነገዶች ላይ እንድትፈርዱ ነው።+ ራእይ 3:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 እኔ ድል ነስቼ ከአባቴ ጋር በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጥኩ ሁሉ+ ድል የሚነሳውንም+ ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ እንዲቀመጥ አደርገዋለሁ።+ ራእይ 20:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ዙፋኖችንም አየሁ፤ በዙፋኖቹም ላይ ለተቀመጡት የመፍረድ ሥልጣን ተሰጣቸው። ስለ ኢየሱስ በመመሥከራቸውና ስለ አምላክ በመናገራቸው የተነሳ የተገደሉትን* ሰዎች ነፍሳት* እንዲሁም አውሬውን ወይም ምስሉን ያላመለኩትንና ምልክቱን በግንባራቸውም ሆነ በእጃቸው ላይ ያልተቀበሉትን ሰዎች አየሁ።+ እነሱም ሕያው ሆነው ከክርስቶስ ጋር ለ1,000 ዓመት ነገሡ።+
28 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “እውነት እላችኋለሁ፣ ሁሉም ነገር አዲስ በሚሆንበት ጊዜ* የሰው ልጅ፣ ክብራማ በሆነው ዙፋኑ ላይ ሲቀመጥ እኔን የተከተላችሁኝ እናንተ በ12 ዙፋኖች ላይ ተቀምጣችሁ በ12ቱ የእስራኤል ነገዶች ላይ ትፈርዳላችሁ።+
28 “ይሁን እንጂ እናንተ በፈተናዎቼ+ ከጎኔ ሳትለዩ ቆይታችኋል፤+ 29 አባቴ ከእኔ ጋር ቃል ኪዳን እንዳደረገ ሁሉ እኔም ከእናንተ ጋር ለመንግሥት ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤+ 30 ይኸውም በመንግሥቴ ከማዕዴ እንድትበሉና እንድትጠጡ+ እንዲሁም በዙፋን ተቀምጣችሁ+ በ12ቱ የእስራኤል ነገዶች ላይ እንድትፈርዱ ነው።+
4 ዙፋኖችንም አየሁ፤ በዙፋኖቹም ላይ ለተቀመጡት የመፍረድ ሥልጣን ተሰጣቸው። ስለ ኢየሱስ በመመሥከራቸውና ስለ አምላክ በመናገራቸው የተነሳ የተገደሉትን* ሰዎች ነፍሳት* እንዲሁም አውሬውን ወይም ምስሉን ያላመለኩትንና ምልክቱን በግንባራቸውም ሆነ በእጃቸው ላይ ያልተቀበሉትን ሰዎች አየሁ።+ እነሱም ሕያው ሆነው ከክርስቶስ ጋር ለ1,000 ዓመት ነገሡ።+