የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኤርምያስ 7
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ኤርምያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • “‘የይሖዋ ቤተ መቅደስ ነው!’ እያላችሁ በአሳሳች ቃል አትታመኑ” (1-11)

      • ቤተ መቅደሱ እንደ ሴሎ ይሆናል (12-15)

      • የሐሰት አምልኮ ተወገዘ (16-34)

        • ‘የሰማይን ንግሥት’ አመለኩ (18)

        • በሂኖም ልጆቻቸውን ሠዉ (31)

ኤርምያስ 7:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 26:13

ኤርምያስ 7:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “እነዚህ።” ይህ ቃል የቤተ መቅደሱን ሕንፃዎች በሙሉ ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሚክ 3:11

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/15/2007፣ ገጽ 10

ኤርምያስ 7:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 21:12፤ 22:3

ኤርምያስ 7:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አባት የሌላቸውን ልጆችና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 24:17፤ መዝ 82:3፤ ዘካ 7:9, 10፤ ያዕ 1:27
  • +ዘዳ 8:19

ኤርምያስ 7:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 30:10፤ ኤር 5:31፤ 14:14

ኤርምያስ 7:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የሚጨስ መሥዋዕት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 3:14፤ ሚክ 2:2
  • +ኤር 5:2
  • +ኤር 11:13

ኤርምያስ 7:10

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ፣

    3/2017፣ ገጽ 3

ኤርምያስ 7:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 21:13፤ ማር 11:17፤ ሉቃስ 19:45, 46

ኤርምያስ 7:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 12:5, 11
  • +ኢያሱ 18:1
  • +1ሳሙ 4:11፤ መዝ 78:60፤ ኤር 26:6, 9

ኤርምያስ 7:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በማለዳ እየተነሳሁ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 36:15, 16፤ ኤር 25:3, 4
  • +ኢሳ 65:12

ኤርምያስ 7:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 25:8, 9
  • +ኤር 7:4
  • +1ሳሙ 4:10, 11፤ መዝ 78:60፤ ኤር 26:4, 6፤ ሰቆ 2:7

ኤርምያስ 7:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 17:22, 23

ኤርምያስ 7:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 15:1
  • +ዘፀ 32:9, 10፤ ኤር 11:14

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    12/1/2001፣ ገጽ 30-31

ኤርምያስ 7:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ከሃዲ እስራኤላውያን የሚያመልኳት አምላክ የማዕረግ ስም ነው፤ የመራባት ሴት አምላክ ልትሆን ትችላለች።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 44:17
  • +ኢሳ 57:6፤ ኤር 19:13፤ ሕዝ 20:28

ኤርምያስ 7:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የሚያስከፉት፤ የሚያስቆጡት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዳን 9:7

ኤርምያስ 7:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሰቆ 2:3
  • +2ነገ 22:17፤ ኤር 17:27

ኤርምያስ 7:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 1:11፤ ኤር 6:20፤ ሆሴዕ 8:13፤ አሞጽ 5:21

ኤርምያስ 7:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 15:22፤ ሆሴዕ 6:6

ኤርምያስ 7:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 19:5፤ ዘሌ 26:3, 12
  • +ዘዳ 5:29

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/15/1999፣ ገጽ 29

ኤርምያስ 7:24

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ምክር።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 32:8
  • +ሆሴዕ 4:16፤ ዘካ 7:12

ኤርምያስ 7:25

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በየዕለቱ በማለዳ እየተነሳሁ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 9:7፤ 1ሳሙ 8:8
  • +2ነገ 17:13፤ 2ዜና 36:15፤ ነህ 9:17, 30፤ ኤር 25:4

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    2/15/1993፣ ገጽ 32

ኤርምያስ 7:26

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “አንገታቸውን አደነደኑ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 33:10፤ ኤር 25:3

ኤርምያስ 7:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 26:2፤ ሕዝ 2:7

ኤርምያስ 7:28

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ከአፋቸው ተቆርጧል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 5:1፤ ሚክ 7:2

ኤርምያስ 7:29

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ለአምላክ የተወሰነውን።”

  • *

    ወይም “የሐዘን እንጉርጉሮ አሰሚ።”

ኤርምያስ 7:30

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 21:1, 4፤ 2ዜና 33:1, 4፤ ኤር 23:11፤ 32:34

ኤርምያስ 7:31

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ፈጽሞ ወደ አእምሮዬ መጥቶ የማያውቀውን።”

  • *

    የቃላት መፍቻው ላይ “ገሃነም” የሚለውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 12:29-31፤ 2ነገ 17:17፤ 2ዜና 28:1, 3፤ 33:1, 6፤ ሕዝ 20:31
  • +ኢያሱ 15:8, 12
  • +ዘሌ 18:21፤ 20:3፤ ኤር 19:5, 6፤ 32:35

ኤርምያስ 7:32

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የቃላት መፍቻው ላይ “ገሃነም” የሚለውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 19:11፤ ሕዝ 6:4, 5

ኤርምያስ 7:33

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 28:26፤ መዝ 79:2፤ ኤር 16:4

ኤርምያስ 7:34

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 24:8፤ ኤር 25:10
  • +ዘሌ 26:33፤ ኢሳ 1:7፤ 6:11

ተዛማጅ ሐሳብ

ኤር. 7:3ኤር 26:13
ኤር. 7:4ሚክ 3:11
ኤር. 7:5ኤር 21:12፤ 22:3
ኤር. 7:6ዘዳ 24:17፤ መዝ 82:3፤ ዘካ 7:9, 10፤ ያዕ 1:27
ኤር. 7:6ዘዳ 8:19
ኤር. 7:8ኢሳ 30:10፤ ኤር 5:31፤ 14:14
ኤር. 7:9ኢሳ 3:14፤ ሚክ 2:2
ኤር. 7:9ኤር 5:2
ኤር. 7:9ኤር 11:13
ኤር. 7:11ማቴ 21:13፤ ማር 11:17፤ ሉቃስ 19:45, 46
ኤር. 7:12ዘዳ 12:5, 11
ኤር. 7:12ኢያሱ 18:1
ኤር. 7:121ሳሙ 4:11፤ መዝ 78:60፤ ኤር 26:6, 9
ኤር. 7:132ዜና 36:15, 16፤ ኤር 25:3, 4
ኤር. 7:13ኢሳ 65:12
ኤር. 7:142ነገ 25:8, 9
ኤር. 7:14ኤር 7:4
ኤር. 7:141ሳሙ 4:10, 11፤ መዝ 78:60፤ ኤር 26:4, 6፤ ሰቆ 2:7
ኤር. 7:152ነገ 17:22, 23
ኤር. 7:16ኤር 15:1
ኤር. 7:16ዘፀ 32:9, 10፤ ኤር 11:14
ኤር. 7:18ኤር 44:17
ኤር. 7:18ኢሳ 57:6፤ ኤር 19:13፤ ሕዝ 20:28
ኤር. 7:19ዳን 9:7
ኤር. 7:20ሰቆ 2:3
ኤር. 7:202ነገ 22:17፤ ኤር 17:27
ኤር. 7:21ኢሳ 1:11፤ ኤር 6:20፤ ሆሴዕ 8:13፤ አሞጽ 5:21
ኤር. 7:221ሳሙ 15:22፤ ሆሴዕ 6:6
ኤር. 7:23ዘፀ 19:5፤ ዘሌ 26:3, 12
ኤር. 7:23ዘዳ 5:29
ኤር. 7:24ዘፀ 32:8
ኤር. 7:24ሆሴዕ 4:16፤ ዘካ 7:12
ኤር. 7:25ዘዳ 9:7፤ 1ሳሙ 8:8
ኤር. 7:252ነገ 17:13፤ 2ዜና 36:15፤ ነህ 9:17, 30፤ ኤር 25:4
ኤር. 7:262ዜና 33:10፤ ኤር 25:3
ኤር. 7:27ኤር 26:2፤ ሕዝ 2:7
ኤር. 7:28ኤር 5:1፤ ሚክ 7:2
ኤር. 7:302ነገ 21:1, 4፤ 2ዜና 33:1, 4፤ ኤር 23:11፤ 32:34
ኤር. 7:31ዘዳ 12:29-31፤ 2ነገ 17:17፤ 2ዜና 28:1, 3፤ 33:1, 6፤ ሕዝ 20:31
ኤር. 7:31ኢያሱ 15:8, 12
ኤር. 7:31ዘሌ 18:21፤ 20:3፤ ኤር 19:5, 6፤ 32:35
ኤር. 7:32ኤር 19:11፤ ሕዝ 6:4, 5
ኤር. 7:33ዘዳ 28:26፤ መዝ 79:2፤ ኤር 16:4
ኤር. 7:34ኢሳ 24:8፤ ኤር 25:10
ኤር. 7:34ዘሌ 26:33፤ ኢሳ 1:7፤ 6:11
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
  • 33
  • 34
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ኤርምያስ 7:1-34

ኤርምያስ

7 ከይሖዋ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፦ 2 “በይሖዋ ቤት በር ላይ ቆመህ በዚያ ይህን መልእክት አውጅ፦ ‘ለይሖዋ ለመስገድ በእነዚህ በሮች የምትገቡ የይሁዳ ሰዎች ሁሉ፣ የይሖዋን ቃል ስሙ። 3 የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “መንገዳችሁንና ተግባራችሁን አስተካክሉ፤ እኔም በዚህ ስፍራ እንድትኖሩ እፈቅድላችኋለሁ።+ 4 ‘ይህ* የይሖዋ ቤተ መቅደስ፣ የይሖዋ ቤተ መቅደስ፣ የይሖዋ ቤተ መቅደስ ነው!’ እያላችሁ በአሳሳች ቃል አትታመኑ።+ 5 በእርግጥ መንገዳችሁንና ተግባራችሁን ብታስተካክሉ፣ በሰውና በባልንጀራው መካከል ፍትሕ ብታሰፍኑ፣+ 6 ከባዕድ አገር የመጣውን ሰው፣ ወላጅ አልባ የሆኑ ልጆችንና* መበለቶችን ባትጨቁኑ፣+ በዚህ ቦታ የንጹሕ ሰው ደም ባታፈሱ እንዲሁም ጉዳት ላይ የሚጥሏችሁን ሌሎች አማልክት ባትከተሉ፣+ 7 በዚህች ስፍራ፣ ለአባቶቻችሁ በሰጠኋቸው በዚህ ምድር ለዘለቄታው እንድትኖሩ እፈቅድላችኋለሁ።”’”

8 “እናንተ ግን አሳሳች በሆነ ቃል ታምናችኋል፤+ ይህ ደግሞ ፈጽሞ አይጠቅማችሁም። 9 እየሰረቃችሁ፣+ እየገደላችሁ፣ እያመነዘራችሁ፣ በሐሰት እየማላችሁ፣+ ለባአል መሥዋዕት* እያቀረባችሁና+ የማታውቋቸውን አማልክት እየተከተላችሁ፣ 10 በስሜ ወደሚጠራው ወደዚህ ቤት መጥታችሁ በፊቴ መቆምና እነዚህን ሁሉ አስጸያፊ ነገሮች እያደረጋችሁ ‘ምንም ችግር አይደርስብንም’ ማለት ትችላላችሁ? 11 ስሜ የሚጠራበት ይህ ቤት በእናንተ ዓይን የዘራፊዎች ዋሻ ሆኗል ማለት ነው?+ እነሆ፣ እኔ ራሴ ይህን አይቻለሁ” ይላል ይሖዋ።

12 “‘አሁን ግን መጀመሪያ የስሜ ማደሪያ+ አድርጌው ወደነበረው በሴሎ+ ወዳለው ስፍራዬ ሂዱ፤ ከሕዝቤ ከእስራኤል ክፋት የተነሳም ምን እንዳደረግኩት እዩ።+ 13 እናንተ ግን እነዚህን ሁሉ ነገሮች መሥራታችሁን ቀጠላችሁ’ ይላል ይሖዋ፤ ‘ለእናንተ ደግሜ ደጋግሜ* ብናገርም እንኳ አልሰማችሁም።+ ደጋግሜ ጠራኋችሁ፤ እናንተ ግን መልስ አትሰጡም።+ 14 ስለዚህ በሴሎ እንዳደረግኩት ሁሉ በስሜ በተጠራው፣+ እናንተም በምትታመኑበት በዚህ ቤት+ ላይ እንዲሁም ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በሰጠሁት በዚህ ቦታ ላይ እንዲሁ አደርጋለሁ።+ 15 ወንድሞቻችሁን ሁሉ ይኸውም መላውን የኤፍሬም ዘር እንዳስወገድኩ እናንተንም ከፊቴ አስወግዳችኋለሁ።’+

16 “አንተም ለዚህ ሕዝብ አትጸልይ። እኔ ስለማልሰማህ+ ስለ እነሱ የልመና ጩኸትም ሆነ ጸሎት አታሰማ ወይም እኔን አትማጸን።+ 17 በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ የሚያደርጉትን አታይም? 18 እኔን ያሳዝኑ ዘንድ ‘ለሰማይ ንግሥት’* መሥዋዕት የሚሆን ቂጣ ለመጋገር ወንዶች ልጆች እንጨት ይሰበስባሉ፣ አባቶች እሳት ያቀጣጥላሉ፣ ሚስቶች ደግሞ ሊጥ ያቦካሉ፤+ ለሌሎች አማልክትም የመጠጥ መባ ያፈሳሉ።+ 19 ‘ለመሆኑ የሚጎዱት* እኔን ነው?’ ይላል ይሖዋ። ‘በራሳቸው ላይ ውርደት በማምጣት የሚጎዱት ራሳቸውን አይደለም?’+ 20 ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ ንዴቴና ቁጣዬ በዚህ ቦታ፣ በሰውና በእንስሳ፣ በዱር ዛፎችና በምድሪቱ ፍሬ ላይ ይፈስሳል፤+ ቁጣዬ ይነድዳል፤ ፈጽሞም አይጠፋም።’+

21 “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የጀመራችሁትን ግፉበት፤ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎቻችሁን በሌሎች መሥዋዕቶቻችሁ ላይ ጨምሩ፤ ሥጋውንም ራሳችሁ ብሉ።+ 22 አባቶቻችሁን ከግብፅ ምድር ባወጣኋቸው ጊዜ ሙሉ በሙሉ ስለሚቃጠሉ መባዎችና መሥዋዕቶች አልነገርኳቸውም ወይም አላዘዝኳቸውም።+ 23 ከዚህ ይልቅ ይህን ትእዛዝ ሰጥቻቸው ነበር፦ “ድምፄን ስሙ፤ እኔም አምላካችሁ እሆናለሁ፤ እናንተም ሕዝቤ ትሆናላችሁ።+ መልካም እንዲሆንላችሁ በማዛችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ።”’+ 24 እነሱ ግን አልሰሙም ወይም ጆሯቸውን አልሰጡም፤+ ይልቁንም ግትር ሆነው ክፉ ልባቸውን በመከተል በገዛ ራሳቸው ዕቅድ* ሄዱ፤+ ወደ ፊት በመሄድ ፋንታ ወደ ኋላ ተመለሱ፤ 25 አባቶቻችሁ ከግብፅ ምድር ከወጡበት ጊዜ አንስቶ እስከዚህ ቀን ድረስ ይህን አደረጉ።+ በመሆኑም አገልጋዮቼ የሆኑትን ነቢያት ሁሉ ወደ እናንተ መላኬን ቀጠልኩ፤ ደግሜ ደጋግሜ በየዕለቱ* ላክኋቸው።+ 26 እነሱ ግን እኔን ለመስማት እንቢተኛ ሆኑ፤ ጆሯቸውንም አልሰጡም።+ ይልቁንም ግትር ሆኑ፤* አባቶቻቸው ከሠሩት የከፋ ነገር አደረጉ!

27 “ይህን ሁሉ ቃል ትነግራቸዋለህ፤+ እነሱ ግን አይሰሙህም፤ ትጠራቸዋለህ፤ እነሱ ግን አይመልሱልህም። 28 እንዲህም ትላቸዋለህ፦ ‘ይህ ብሔር የአምላኩን የይሖዋን ድምፅ አልሰማም፤ ተግሣጽ ለመቀበልም እንቢተኛ ሆኗል። ታማኝነት ጠፍቷል፤ በመካከላቸውም ጨርሶ አይነሳም።’*+

29 “ያልተቆረጠውን* ፀጉርሽን ሸልተሽ ጣይው፤ በተራቆቱት ኮረብቶችም ላይ ሙሾ አውርጂ፤* ይሖዋ እጅግ ያስቆጣውን ይህን ትውልድ ጥሎታልና፤ እርግፍ አድርጎም ይተወዋል። 30 ‘የይሁዳ ሰዎች በፊቴ መጥፎ ነገር ሠርተዋልና’ ይላል ይሖዋ። ‘አስጸያፊ ጣዖቶቻቸውን በስሜ በተጠራው ቤት ውስጥ በማስቀመጥ አርክሰውታል።+ 31 ያላዘዝኩትንና በልቤ እንኳ ፈጽሞ ያላሰብኩትን* ነገር ለማድረግ ይኸውም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በእሳት ለማቃጠል+ በሂኖም ልጅ ሸለቆ*+ የሚገኘውን የቶፌትን ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎች ሠርተዋል።’+

32 “‘ከዚህ የተነሳ፣’ ይላል ይሖዋ፣ ‘የእርድ ሸለቆ እንጂ ቶፌት ወይም የሂኖም ልጅ ሸለቆ* ተብሎ የማይጠራበት ጊዜ ይመጣል። እነሱም ቦታ እስኪታጣ ድረስ በቶፌት ይቀብራሉ።+ 33 የዚህ ሕዝብ አስከሬንም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ሲሳይ ይሆናል፤ ፈርተው እንዲሸሹ የሚያደርጋቸውም የለም።+ 34 የሐሴትንና የደስታን ድምፅ እንዲሁም የሙሽራንና የሙሽሪትን ድምፅ፣ ከይሁዳ ከተሞችና ከኢየሩሳሌም ጎዳናዎች አጠፋለሁ፤+ ምድሪቱ የፍርስራሽ ክምር ትሆናለችና።’”+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ