የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መዝሙር 116
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

መዝሙር የመጽሐፉ ይዘት

      • የምስጋና መዝሙር

        • “ለይሖዋ ምን እመልስለታለሁ?” (12)

        • “የማዳንን ጽዋ አነሳለሁ” (13)

        • “ስእለቴን ለይሖዋ እፈጽማለሁ” (14, 18)

        • የአገልጋዮቹ ሞት በይሖዋ ዓይን ከባድ ነገር ነው (15)

መዝሙር 116:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ይሖዋ ስለሚሰማ ውስጤ በፍቅር ይሞላል” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 18:6

መዝሙር 116:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ጎንበስ ብሎ ይሰማኛልና።”

  • *

    ቃል በቃል “በቀኖቼ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 34:15

መዝሙር 116:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የሲኦል ጭንቅ አገኘኝ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 38:10
  • +መዝ 18:4፤ 38:6

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣

    8/2016፣ ገጽ 1

መዝሙር 116:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሴን ታደግ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 34:6፤ ሮም 10:13

መዝሙር 116:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቸርና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 32:4
  • +ዘፀ 34:6፤ ነህ 9:17፤ ዳን 9:9

መዝሙር 116:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 19:7

መዝሙር 116:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

መዝሙር 116:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሴን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 56:13፤ 94:18

መዝሙር 116:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ቆሮ 4:13

መዝሙር 116:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 3:4

መዝሙር 116:12

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/15/2009፣ ገጽ 29

    12/1/1998፣ ገጽ 24

መዝሙር 116:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 22:25፤ ዮናስ 2:9

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/15/2009፣ ገጽ 29

መዝሙር 116:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ክቡር።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 25:29፤ ኢዮብ 1:12፤ መዝ 91:14፤ ዘካ 2:8፤ 2ጴጥ 2:9

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/15/2012፣ ገጽ 30

    5/15/2012፣ ገጽ 22

    9/1/2006፣ ገጽ 14

መዝሙር 116:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 107:14

መዝሙር 116:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 7:12፤ መዝ 50:23

መዝሙር 116:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 22:25፤ 76:11፤ 116:14

መዝሙር 116:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 96:8
  • +ራእይ 19:1

ተዛማጅ ሐሳብ

መዝ. 116:1መዝ 18:6
መዝ. 116:2መዝ 34:15
መዝ. 116:3ኢሳ 38:10
መዝ. 116:3መዝ 18:4፤ 38:6
መዝ. 116:4መዝ 34:6፤ ሮም 10:13
መዝ. 116:5ዘዳ 32:4
መዝ. 116:5ዘፀ 34:6፤ ነህ 9:17፤ ዳን 9:9
መዝ. 116:6መዝ 19:7
መዝ. 116:8መዝ 56:13፤ 94:18
መዝ. 116:102ቆሮ 4:13
መዝ. 116:11ሮም 3:4
መዝ. 116:14መዝ 22:25፤ ዮናስ 2:9
መዝ. 116:151ሳሙ 25:29፤ ኢዮብ 1:12፤ መዝ 91:14፤ ዘካ 2:8፤ 2ጴጥ 2:9
መዝ. 116:16መዝ 107:14
መዝ. 116:17ዘሌ 7:12፤ መዝ 50:23
መዝ. 116:18መዝ 22:25፤ 76:11፤ 116:14
መዝ. 116:19መዝ 96:8
መዝ. 116:19ራእይ 19:1
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
መዝሙር 116:1-19

መዝሙር

116 ይሖዋ ድምፄን፣

እርዳታ ለማግኘት የማቀርበውን ልመና ስለሚሰማ እወደዋለሁ።*+

 2 ጆሮውን ወደ እኔ ያዘነብላልና፣*+

በሕይወት እስካለሁ ድረስ* እሱን እጣራለሁ።

 3 የሞት ገመዶች ተተበተቡብኝ፤

መቃብር ያዘኝ።*+

በጭንቀትና በሐዘን ተዋጥኩ።+

 4 እኔ ግን የይሖዋን ስም ጠራሁ፦+

“ይሖዋ ሆይ፣ ታደገኝ!”*

 5 ይሖዋ ሩኅሩኅና* ጻድቅ ነው፤+

አምላካችን መሐሪ ነው።+

 6 ይሖዋ ተሞክሮ የሌላቸውን ይጠብቃል።+

ተስፋ ቆርጬ ነበር፤ እሱ ግን አዳነኝ።

 7 ነፍሴ* ዳግመኛ እረፍት ታግኝ፤

ይሖዋ ደግነት አሳይቶኛልና።

 8 እኔን* ከሞት፣ ዓይኔን ከእንባ፣

እግሬንም ከእንቅፋት ታድገሃል።+

 9 በሕያዋን ምድር በይሖዋ ፊት እሄዳለሁ።

10 አመንኩ ስለዚህም ተናገርኩ፤+

እጅግ ተጎሳቁዬ ነበር።

11 በጣም ደንግጬ

“ሰው ሁሉ ውሸታም ነው”+ አልኩ።

12 ላደረገልኝ መልካም ነገር ሁሉ

ለይሖዋ ምን እመልስለታለሁ?

13 የማዳንን ጽዋ አነሳለሁ፤

የይሖዋንም ስም እጠራለሁ።

14 በሕዝቡ ሁሉ ፊት

ስእለቴን ለይሖዋ እፈጽማለሁ።+

15 የታማኝ አገልጋዮቹ ሞት

በይሖዋ ዓይን ከባድ ነገር* ነው።+

16 ይሖዋ ሆይ፣

እኔ አገልጋይህ ስለሆንኩ እለምንሃለሁ።

እኔ የሴት ባሪያህ ልጅ፣ አገልጋይህ ነኝ።

አንተ ከእስራቴ ነፃ አውጥተኸኛል።+

17 ለአንተ የምስጋና መሥዋዕት አቀርባለሁ፤+

የይሖዋን ስም እጠራለሁ።

18 በሕዝቡ ሁሉ ፊት፣

ስእለቴን ለይሖዋ እፈጽማለሁ፤+

19 በይሖዋ ቤት ቅጥር ግቢዎች፣+

በኢየሩሳሌም መካከል ስእለቴን አቀርባለሁ።

ያህን አወድሱ!*+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ