የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ዜና መዋዕል 13
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

1 ዜና መዋዕል የመጽሐፉ ይዘት

      • ታቦቱ ከቂርያትየአሪም መጣ (1-14)

        • ዖዛ ተቀሰፈ (9, 10)

1 ዜና መዋዕል 13:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 15:25

1 ዜና መዋዕል 13:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 35:2

1 ዜና መዋዕል 13:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 7:2
  • +1ሳሙ 14:18

1 ዜና መዋዕል 13:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ከሺሆር።”

  • *

    ወይም “እስከ ሃማት መግቢያ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 34:2, 8
  • +1ሳሙ 6:21-7:1፤ 2ሳሙ 6:1, 2፤ 1ዜና 15:3

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/1/2005፣ ገጽ 10

1 ዜና መዋዕል 13:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “በኪሩቤል መካከል” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 25:22፤ ዘኁ 7:89፤ 1ሳሙ 4:4፤ 2ሳሙ 6:2
  • +ኢያሱ 15:9, 12

1 ዜና መዋዕል 13:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 37:5
  • +2ሳሙ 6:3-8

1 ዜና መዋዕል 13:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    እዚህ ላይ የገባው የዕብራይስጥ ቃል፣ እርስ በርሱ ሲጋጭ ኃይለኛ ድምፅ የሚያወጣን ክብ ቅርጽ ያለው ከብረት የተሠራ የሙዚቃ መሣሪያ ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 15:20
  • +1ዜና 25:1
  • +2ዜና 5:13

1 ዜና መዋዕል 13:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 4:15
  • +ዘሌ 10:1, 2

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    2/1/2005፣ ገጽ 26-27

1 ዜና መዋዕል 13:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አዘነ።”

  • *

    “በዖዛ ላይ መገንፈል” የሚል ትርጉም አለው።

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/1/2005፣ ገጽ 11

1 ዜና መዋዕል 13:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 6:9-11

1 ዜና መዋዕል 13:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 30:27፤ 39:5

ተዛማጅ ሐሳብ

1 ዜና 13:11ዜና 15:25
1 ዜና 13:2ዘኁ 35:2
1 ዜና 13:31ሳሙ 7:2
1 ዜና 13:31ሳሙ 14:18
1 ዜና 13:5ዘኁ 34:2, 8
1 ዜና 13:51ሳሙ 6:21-7:1፤ 2ሳሙ 6:1, 2፤ 1ዜና 15:3
1 ዜና 13:6ዘፀ 25:22፤ ዘኁ 7:89፤ 1ሳሙ 4:4፤ 2ሳሙ 6:2
1 ዜና 13:6ኢያሱ 15:9, 12
1 ዜና 13:7ዘፀ 37:5
1 ዜና 13:72ሳሙ 6:3-8
1 ዜና 13:8ዘፀ 15:20
1 ዜና 13:81ዜና 25:1
1 ዜና 13:82ዜና 5:13
1 ዜና 13:10ዘኁ 4:15
1 ዜና 13:10ዘሌ 10:1, 2
1 ዜና 13:122ሳሙ 6:9-11
1 ዜና 13:14ዘፍ 30:27፤ 39:5
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
1 ዜና መዋዕል 13:1-14

አንደኛ ዜና መዋዕል

13 ዳዊት ከሺህ አለቆቹና ከመቶ አለቆቹ እንዲሁም ከመሪዎቹ ሁሉ ጋር ተማከረ።+ 2 ከዚያም ዳዊት ለመላው የእስራኤል ጉባኤ እንዲህ አለ፦ “ነገሩ መልካም መስሎ ከታያችሁና በአምላካችን በይሖዋ ፊት ተቀባይነት ያለው ከሆነ፣ በእስራኤል ምድር ሁሉ ያሉት የቀሩት ወንድሞቻችን እንዲሁም የግጦሽ መሬቶች ባሏቸው ከተሞቻቸው የሚኖሩት ካህናትና ሌዋውያን+ ወደ እኛ እንዲሰበሰቡ መልእክት እንላክባቸው። 3 የአምላካችንንም ታቦት መልሰን እናምጣ።”+ በሳኦል ዘመን ታቦቱን ችላ ብለውት ነበርና።+ 4 ነገሩ በሕዝቡ ሁሉ ፊት መልካም ሆኖ ስለተገኘ መላው ጉባኤ ይህን ለማድረግ ተስማማ። 5 በመሆኑም ዳዊት የእውነተኛውን አምላክ ታቦት ከቂርያትየአሪም ለማምጣት ከግብፅ ወንዝ* አንስቶ እስከ ሌቦሃማት*+ ድረስ ያለውን የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ሰበሰበ።+

6 ዳዊትና መላው የእስራኤል ሕዝብ ከኪሩቤል በላይ* በዙፋን የሚቀመጠውን+ የእውነተኛውን አምላክ ታቦት ይኸውም ሰዎች የይሖዋን ስም የሚጠሩበትን ታቦት ለማምጣት በይሁዳ ምድር ወደምትገኘው ቂርያትየአሪም ወደምትባለው ወደ ባዓላ+ ወጡ። 7 ይሁን እንጂ የእውነተኛውን አምላክ ታቦት በአዲስ ሠረገላ ላይ ጭነው+ ከአቢናዳብ ቤት አመጡት፤ ደግሞም ዖዛና አሂዮ ሠረገላውን እየነዱ ነበር።+ 8 ዳዊትና መላው የእስራኤል ሕዝብ በመዝሙር፣ በበገና፣ በባለ አውታር መሣሪያዎች፣ በአታሞ፣+ በሲምባልና*+ በመለከት+ ታጅበው በሙሉ ኃይላቸው በእውነተኛው አምላክ ፊት በደስታ ይጨፍሩ ነበር። 9 ወደ ኪዶን አውድማ ሲደርሱ ግን ከብቶቹ ታቦቱን ሊጥሉት ተቃርበው ስለነበር ዖዛ እጁን ዘርግቶ ታቦቱን ያዘ። 10 በዚህ ጊዜ የይሖዋ ቁጣ በዖዛ ላይ ነደደ፤ ታቦቱን ለመያዝ እጁን በመዘርጋቱም ቀሰፈው፤+ እሱም በአምላክ ፊት እዚያው ሞተ።+ 11 ሆኖም የይሖዋ ቁጣ በዖዛ ላይ ስለነደደ ዳዊት ተበሳጨ፤* ያም ቦታ እስከ ዛሬ ድረስ ጴሬዝዖዛ* ተብሎ ይጠራል።

12 ዳዊትም በዚያን ዕለት እውነተኛውን አምላክ ፈርቶ “ታዲያ የእውነተኛውን አምላክ ታቦት እንዴት ወደ እኔ ማምጣት እችላለሁ?” አለ።+ 13 ዳዊት ታቦቱን እሱ ወዳለበት ወደ ዳዊት ከተማ አላመጣውም፤ ይልቁንም የጌት ሰው ወደሆነው ወደ ኦቤድዔዶም ቤት እንዲወሰድ አደረገ። 14 የእውነተኛው አምላክ ታቦት ከኦቤድዔዶም ቤተሰብ ጋር በቤቱ ለሦስት ወራት ያህል ተቀመጠ፤ ይሖዋም የኦቤድዔዶምን ቤተሰብና ያለውን ሁሉ ባረከ።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ