መዝሙር
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የቆሬ ልጆች+ ማህሌት።
47 እናንተ ሕዝቦች ሁሉ፣ እጆቻችሁን አጨብጭቡ።
በድል አድራጊነት ለአምላክ እልል በሉ።
3 ሕዝቦችን ለእኛ ያስገዛል፤
ብሔራትም ከእግራችን በታች እንዲሆኑ ያደርጋል።+
5 አምላክ በእልልታ አረገ፤
ይሖዋ በቀንደ መለከት* ድምፅ ወደ ላይ ወጣ።
6 ለአምላክ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ፤ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ።
ለንጉሣችን የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ፤ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ።
7 አምላክ የምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና፤+
የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ፤ ማስተዋልም ይኑራችሁ።
8 አምላክ በብሔራት ላይ ነግሦአል።+
በቅዱስ ዙፋኑ ላይ ተቀምጧል።
9 የሕዝቡ መሪዎች ከአብርሃም አምላክ ሕዝብ ጋር
አንድ ላይ ተሰብስበዋል።
የምድር ገዢዎች* የአምላክ ናቸውና።
እሱ እጅግ ከፍ ከፍ ብሏል።+