ኢሳይያስ
የሞዓብ ኤር+ በሌሊት ስለወደመች
ጸጥ ረጭ ብላለች።
የሞዓብ ቂር+ በሌሊት ስለወደመች
ጸጥ ረጭ ብላለች።
ሞዓብ ስለ ነቦና+ ስለ መደባ+ ዋይ ዋይ ይላል።
3 በጎዳናዎቹ ላይ ማቅ ለብሰው ይታያሉ።
ሁሉም በጣሪያዎቻቸውና በአደባባዮቻቸው ላይ ዋይ ዋይ ይላሉ፤
እያለቀሱም ይወርዳሉ።+
ከዚህም የተነሳ የሞዓብ ተዋጊዎች ይጮኻሉ።
እሱም* ይንቀጠቀጣል።
5 ልቤ ስለ ሞዓብ ያለቅሳል።
የሚሸሹት የሞዓብ ሰዎች እስከ ዞአርና+ እስከ ኤግላት ሸሊሺያ+ ድረስ ተሰደዱ።
እያለቀሱ የሉሂትን ዳገት ይወጣሉ፤
በደረሰባቸው ድንገተኛ ጥፋት የተነሳ ወደ ሆሮናይም በሚወስደው መንገድ ላይ ሲሄዱ ይጮኻሉ።+
7 በመሆኑም ካከማቹት ንብረት ውስጥ የተረፈውን እንዲሁም ሀብታቸውን ተሸክመው
የአኻያ ዛፎች የሚገኙበትን ሸለቆ* ይሻገራሉ።
8 ጩኸታቸው እስከ ሞዓብ ወሰን ድረስ አስተጋብቷል።+
ዋይታቸው እስከ ኤግላይም፣
እስከ በኤርዔሊም ድረስም ተሰምቷል።
9 የዲሞን ውኃዎች በደም ተሞልተዋልና፤
በዲሞንም ላይ ተጨማሪ ነገሮች አመጣለሁ፦
በሚሸሹት ሞዓባውያንና
በምድሪቱ ላይ በሚቀሩት ሰዎች ላይ አንበሶች እሰዳለሁ።+