የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መዝሙር 44
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

መዝሙር የመጽሐፉ ይዘት

      • እርዳታ ለማግኘት የቀረበ ጸሎት

        • ‘ያዳንከን አንተ ነህ’ (7)

        • ‘እንደ እርድ በጎች ተቆጠርን’ (22)

        • “እኛን ለመርዳት ተነስ!” (26)

መዝሙር 44:በመዝሙሩ አናት ላይ የሚገኘው መግለጫ

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 20:19

መዝሙር 44:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 13:14፤ ዘኁ 21:14፤ መሳ 6:13

መዝሙር 44:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 7:1
  • +ዘፀ 15:17፤ መዝ 78:55፤ 80:8, 9
  • +ኢያሱ 10:5, 11፤ መዝ 135:10, 11

መዝሙር 44:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 4:38፤ ኢያሱ 24:12
  • +1ሳሙ 12:22
  • +ዘዳ 7:7, 8
  • +ኢሳ 63:11-13

መዝሙር 44:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ታላቅ መዳን።”

  • *

    ወይም “አጎናጽፍ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 74:12፤ ኢሳ 33:22

መዝሙር 44:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 18:39፤ ፊልጵ 4:13
  • +መዝ 60:12

መዝሙር 44:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 17:45፤ መዝ 20:7፤ 33:16

መዝሙር 44:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 24:8

መዝሙር 44:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 28:15, 25

መዝሙር 44:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 28:64

መዝሙር 44:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 32:30

መዝሙር 44:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “መተረቻ እንድንሆን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 28:37፤ 2ዜና 7:20

መዝሙር 44:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 34:10

መዝሙር 44:19

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/1/2006፣ ገጽ 8

መዝሙር 44:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 139:1፤ መክ 12:14፤ ኤር 17:10

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 36

መዝሙር 44:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 8:36

መዝሙር 44:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 7:6፤ 78:65, 66
  • +ኢዮብ 13:24፤ መዝ 13:1፤ 88:14

መዝሙር 44:25

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሳችን ወደ አፈር ተጥላለችና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 119:25

መዝሙር 44:26

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ዋጀን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 33:20
  • +መዝ 130:7

ተዛማጅ ሐሳብ

መዝ. 44:በመዝሙሩ አናት ላይ የሚገኘው መግለጫ2ዜና 20:19
መዝ. 44:1ዘፀ 13:14፤ ዘኁ 21:14፤ መሳ 6:13
መዝ. 44:2ዘዳ 7:1
መዝ. 44:2ዘፀ 15:17፤ መዝ 78:55፤ 80:8, 9
መዝ. 44:2ኢያሱ 10:5, 11፤ መዝ 135:10, 11
መዝ. 44:3ዘዳ 4:38፤ ኢያሱ 24:12
መዝ. 44:31ሳሙ 12:22
መዝ. 44:3ዘዳ 7:7, 8
መዝ. 44:3ኢሳ 63:11-13
መዝ. 44:4መዝ 74:12፤ ኢሳ 33:22
መዝ. 44:5መዝ 18:39፤ ፊልጵ 4:13
መዝ. 44:5መዝ 60:12
መዝ. 44:61ሳሙ 17:45፤ መዝ 20:7፤ 33:16
መዝ. 44:7ኢያሱ 24:8
መዝ. 44:10ዘዳ 28:15, 25
መዝ. 44:11ዘዳ 28:64
መዝ. 44:12ዘዳ 32:30
መዝ. 44:14ዘዳ 28:37፤ 2ዜና 7:20
መዝ. 44:17ዘፀ 34:10
መዝ. 44:21መዝ 139:1፤ መክ 12:14፤ ኤር 17:10
መዝ. 44:22ሮም 8:36
መዝ. 44:23መዝ 7:6፤ 78:65, 66
መዝ. 44:23ኢዮብ 13:24፤ መዝ 13:1፤ 88:14
መዝ. 44:25መዝ 119:25
መዝ. 44:26መዝ 33:20
መዝ. 44:26መዝ 130:7
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
መዝሙር 44:1-26

መዝሙር

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የቆሬ ልጆች መዝሙር።+ ማስኪል።*

44 አምላክ ሆይ፣ በገዛ ጆሯችን ሰምተናል፤

ከረጅም ጊዜ በፊት፣

በእነሱ ዘመን ያከናወንካቸውን ተግባሮች፣

አባቶቻችን ተርከውልናል።+

 2 በእጅህ ብሔራትን አባረርክ፤+

በዚያም አባቶቻችንን አሰፈርክ።+

ብሔራትን ድል አድርገህ አባረርካቸው።+

 3 ምድሪቱን የወረሱት በገዛ ሰይፋቸው አይደለም፤+

ድል ያጎናጸፋቸውም የገዛ ክንዳቸው አይደለም።+

ከዚህ ይልቅ በእነሱ ደስ ስለተሰኘህ+

ቀኝ እጅህ፣ ክንድህና የፊትህ ብርሃን ይህን አድርጓል።+

 4 አምላክ ሆይ፣ አንተ ንጉሤ ነህ፤+

ለያዕቆብ ፍጹም ድል* እዘዝ።*

 5 በአንተ ኃይል ጠላቶቻችንን እንመክታለን፤+

በእኛ ላይ የተነሱትን በስምህ እንረግጣለን።+

 6 በቀስቴ አልታመንምና፤

ሰይፌም ሊያድነኝ አይችልም።+

 7 ከጠላቶቻችን ያዳንከን፣

የሚጠሉንን ሰዎች ያዋረድካቸው አንተ ነህ።+

 8 ቀኑን ሙሉ ለአምላክ ውዳሴ እናቀርባለን፤

ስምህንም ለዘላለም እናመሰግናለን። (ሴላ)

 9 አሁን ግን ትተኸናል፤ ደግሞም አዋርደኸናል፤

ከሠራዊታችንም ጋር አብረህ አትወጣም።

10 ከጠላታችን ፊት እንድንሸሽ ታደርገናለህ፤+

የሚጠሉን ሰዎች የፈለጉትን ሁሉ ይወስዱብናል።

11 እንደ በግ እንዲበሉን ለጠላቶቻችን አሳልፈህ ሰጠኸን፤

በብሔራት መካከል በተንከን።+

12 ሕዝብህን በማይረባ ዋጋ ሸጥክ፤+

ከሽያጩ ያገኘኸው ትርፍ የለም።

13 በጎረቤቶቻችን ዘንድ መሳለቂያ አደረግከን፤

በዙሪያችን ያሉት ሁሉ እንዲያላግጡብንና እንዲዘብቱብን አደረግክ።

14 በብሔራት መካከል መቀለጃ እንድንሆን፣*

ሕዝቦችም ራሳቸውን እንዲነቀንቁብን አደረግክ።+

15 ቀኑን ሙሉ በኀፍረት ተውጫለሁ፤

ውርደትም ተከናንቤአለሁ፤

16 ይህም ከሚሳለቁና ከሚሳደቡ ሰዎች ድምፅ፣

እንዲሁም ከሚበቀለን ጠላታችን የተነሳ ነው።

17 ይህ ሁሉ በእኛ ላይ ደርሷል፤ እኛ ግን አልረሳንህም፤

ቃል ኪዳንህንም አላፈረስንም።+

18 ልባችን አልሸፈተም፤

እግራችንም ከመንገድህ አልወጣም።

19 ይሁንና ቀበሮዎች በሚኖሩበት ቦታ ሰባብረኸናል፤

በድቅድቅ ጨለማም ሸፍነኸናል።

20 የአምላካችንን ስም ረስተን፣

ወይም ወደ ባዕድ አምላክ ለመጸለይ እጃችንን ዘርግተን ከሆነ፣

21 አምላክ ይህን አይደርስበትም?

እሱ በልብ ውስጥ ያለውን ሚስጥር ያውቃል።+

22 ስለ አንተ ቀኑን ሙሉ ሞትን እንጋፈጣለን፤

እንደ እርድ በጎችም ተቆጠርን።+

23 ይሖዋ ሆይ፣ ተነስ። ለምንስ ትተኛለህ?+

ንቃ! ለዘላለም አትጣለን።+

24 ፊትህን ለምን ትሰውራለህ?

የደረሰብንን ጉስቁልናና ጭቆና የምትረሳው ለምንድን ነው?

25 ወደ አፈር ተጥለናልና፤*

ሰውነታችን ከመሬት ጋር ተጣብቋል።+

26 እኛን ለመርዳት ተነስ!+

ስለ ታማኝ ፍቅርህ ስትል ታደገን።*+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ