የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ዜና መዋዕል 22
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

2 ዜና መዋዕል የመጽሐፉ ይዘት

      • አካዝያስ በይሁዳ ላይ ነገሠ (1-9)

      • ጎቶልያ በጉልበት ዙፋን ላይ ወጣች (10-12)

2 ዜና መዋዕል 22:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    በ2ዜና 21:17 ላይ ኢዮዓካዝ ተብሎም ተጠርቷል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 21:16, 17
  • +2ነገ 8:24-26

2 ዜና መዋዕል 22:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ሴት ልጅ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 11:1, 13, 16፤ 2ዜና 24:7
  • +1ነገ 16:28

2 ዜና መዋዕል 22:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 16:33፤ 2ነገ 8:27, 28፤ ሚክ 6:16

2 ዜና መዋዕል 22:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 8:15፤ 10:32
  • +1ነገ 22:3፤ 2ዜና 18:14

2 ዜና መዋዕል 22:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    በአንዳንድ የዕብራይስጥ ጥንታዊ ቅጂዎች ላይ አዛርያስ ተብሎም ተጠርቷል።

  • *

    ወይም “ታሞ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 9:15
  • +ኢያሱ 19:18, 23
  • +2ነገ 3:1
  • +2ነገ 8:16
  • +2ነገ 9:16

2 ዜና መዋዕል 22:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ወንድ ልጅ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 19:16፤ 2ነገ 9:20, 21
  • +2ነገ 9:6, 7

2 ዜና መዋዕል 22:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 10:10-14

2 ዜና መዋዕል 22:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 9:27, 28፤ 2ዜና 17:3, 4

2 ዜና መዋዕል 22:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የመንግሥት ዘር።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 22:2
  • +2ነገ 11:1-3

2 ዜና መዋዕል 22:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 11:21
  • +2ነገ 8:16
  • +2ዜና 23:1
  • +2ሳሙ 7:12, 13፤ 1ነገ 15:4፤ 2ዜና 21:7

ተዛማጅ ሐሳብ

2 ዜና 22:12ዜና 21:16, 17
2 ዜና 22:12ነገ 8:24-26
2 ዜና 22:22ነገ 11:1, 13, 16፤ 2ዜና 24:7
2 ዜና 22:21ነገ 16:28
2 ዜና 22:31ነገ 16:33፤ 2ነገ 8:27, 28፤ ሚክ 6:16
2 ዜና 22:52ነገ 8:15፤ 10:32
2 ዜና 22:51ነገ 22:3፤ 2ዜና 18:14
2 ዜና 22:62ነገ 9:15
2 ዜና 22:6ኢያሱ 19:18, 23
2 ዜና 22:62ነገ 3:1
2 ዜና 22:62ነገ 8:16
2 ዜና 22:62ነገ 9:16
2 ዜና 22:71ነገ 19:16፤ 2ነገ 9:20, 21
2 ዜና 22:72ነገ 9:6, 7
2 ዜና 22:82ነገ 10:10-14
2 ዜና 22:92ነገ 9:27, 28፤ 2ዜና 17:3, 4
2 ዜና 22:102ዜና 22:2
2 ዜና 22:102ነገ 11:1-3
2 ዜና 22:112ነገ 11:21
2 ዜና 22:112ነገ 8:16
2 ዜና 22:112ዜና 23:1
2 ዜና 22:112ሳሙ 7:12, 13፤ 1ነገ 15:4፤ 2ዜና 21:7
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
2 ዜና መዋዕል 22:1-12

ሁለተኛ ዜና መዋዕል

22 ከዚያም የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች የመጨረሻ ልጁን አካዝያስን* በእሱ ምትክ አነገሡት፤ ከዓረቦቹ ጋር ወደ ሰፈሩ የመጡት ወራሪዎች ታላላቆቹን በሙሉ ገድለዋቸው ነበር።+ በመሆኑም የኢዮራም ልጅ አካዝያስ የይሁዳ ንጉሥ ሆኖ መግዛት ጀመረ።+ 2 አካዝያስ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 22 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ አንድ ዓመት ገዛ። እናቱም ጎቶልያ+ የተባለች የኦምሪ+ የልጅ ልጅ* ነበረች።

3 እናቱ ክፉ ነገር እንዲያደርግ ትመክረው ስለነበር እሱም የአክዓብን+ ቤት መንገድ ተከተለ። 4 ከአባቱ ሞት በኋላ የአክዓብ ቤት ሰዎች አማካሪዎቹ በመሆን ወደ ጥፋት ስለመሩት ልክ እንደ አክዓብ ቤት እሱም በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር ማድረጉን ቀጠለ። 5 እሱም የእነሱን ምክር ተከትሎ ከሶርያ ንጉሥ ከሃዛኤል+ ጋር በራሞትጊልያድ+ ለመዋጋት ከእስራኤል ንጉሥ ከአክዓብ ልጅ ከኢዮራም ጋር ሄደ፤ በዚያም ቀስተኞች ኢዮራምን አቆሰሉት። 6 እሱም ከሶርያ ንጉሥ ከሃዛኤል ጋር በተዋጋበት ጊዜ+ በራማ ካቆሰሉት ቁስል ለማገገም ወደ ኢይዝራኤል+ ተመለሰ።

የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራም+ ልጅ አካዝያስ* የአክዓብ ልጅ ኢዮራም+ ቆስሎ*+ ስለነበር እሱን ለማየት ወደ ኢይዝራኤል ወረደ። 7 ይሁንና አካዝያስ ወደ ኢዮራም በመምጣቱ አምላክ ለውድቀት ዳረገው፤ እዚያ ከደረሰ በኋላም ከኢዮራም ጋር የኒምሺን የልጅ ልጅ* ኢዩን+ ለማግኘት ሄዱ፤ ኢዩ የአክዓብን ቤት እንዲያጠፋ ይሖዋ የቀባው ሰው ነበር።+ 8 ኢዩም በአክዓብ ቤት ላይ የተላለፈውን ፍርድ ማስፈጸም ሲጀምር የአካዝያስ አገልጋዮች የነበሩትን የይሁዳን መኳንንትና የአካዝያስን ወንድሞች ልጆች አግኝቶ ገደላቸው።+ 9 ከዚያም አካዝያስን ለመፈለግ ሄደ፤ እነሱም በሰማርያ ተደብቆ ሳለ ያዙት፤ ወደ ኢዩም አመጡት። ከዚያም ገደሉት፤ ይሁንና “ይሖዋን በሙሉ ልቡ የፈለገው የኢዮሳፍጥ የልጅ ልጅ ነው” በማለት ቀበሩት።+ ከአካዝያስ ቤት የመንግሥቱን ሥልጣን የመያዝ ብቃት ያለው ሰው አልነበረም።

10 የአካዝያስ እናት ጎቶልያ+ ልጇ መሞቱን ባየች ጊዜ ተነስታ የይሁዳን ንጉሣውያን ቤተሰብ* በሙሉ አጠፋች።+ 11 ይሁንና የንጉሡ ልጅ የሆነችው ዮሳቤት ሊገደሉ ከነበሩት የንጉሡ ልጆች መካከል የአካዝያስን ልጅ ኢዮዓስን+ ሰርቃ በመውሰድ እሱንና ሞግዚቱን በውስጠኛው መኝታ ክፍል አስቀመጠቻቸው። የንጉሥ ኢዮራም+ ልጅ የሆነችው ዮሳቤት (የካህኑ ዮዳሄ+ ሚስትና የአካዝያስ እህት ነበረች) ከጎቶልያ ደብቃ አቆየችው፤ በመሆኑም ጎቶልያ ሳትገድለው ቀረች።+ 12 እሱም ከእነሱ ጋር ለስድስት ዓመት በእውነተኛው አምላክ ቤት ተደብቆ ቆየ፤ በዚህ ጊዜ ጎቶልያ በምድሪቱ ላይ ትገዛ ነበር።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ