የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ዜና መዋዕል 23
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

2 ዜና መዋዕል የመጽሐፉ ይዘት

      • ካህኑ ዮዳሄ ድፍረት የተሞላበት እርምጃ ወሰደ፤ ኢዮዓስ ነገሠ (1-11)

      • ጎቶልያ ተገደለች (12-15)

      • ዮዳሄ ያካሄደው ተሃድሶ (16-21)

2 ዜና መዋዕል 23:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቃል ኪዳን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 11:4

2 ዜና መዋዕል 23:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 8:14

2 ዜና መዋዕል 23:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 5:3
  • +2ሳሙ 7:8, 12፤ 1ነገ 2:4፤ 9:5፤ መዝ 89:20, 29

2 ዜና መዋዕል 23:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 24:3
  • +2ነገ 11:5-8፤ 1ዜና 9:22-25፤ 26:1

2 ዜና መዋዕል 23:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቤተ መንግሥት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 7:1
  • +1ነገ 7:12

2 ዜና መዋዕል 23:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 23:28, 32

2 ዜና መዋዕል 23:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በሚወጣበትም ሆነ በሚገባበት ጊዜ።”

2 ዜና መዋዕል 23:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 11:9-12
  • +1ዜና 24:1፤ 26:1

2 ዜና መዋዕል 23:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    አብዛኛውን ጊዜ ቀስተኞች የሚይዙት ትንሽ ጋሻ።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 26:26, 27፤ 2ዜና 5:1
  • +2ሳሙ 8:7
  • +2ነገ 11:4

2 ዜና መዋዕል 23:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ተወንጫፊ መሣሪያቸውን።”

2 ዜና መዋዕል 23:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ዘውዱን።”

  • *

    የአምላክ ሕግ የሰፈረበት ጥቅልል ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 11:2
  • +ዘዳ 17:18
  • +1ሳሙ 10:1, 24

2 ዜና መዋዕል 23:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 11:13-16

2 ዜና መዋዕል 23:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ውዳሴ እንዲቀርብ ምልክት ይሰጡ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 23:1
  • +1ነገ 1:39, 40

2 ዜና መዋዕል 23:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቤተ መንግሥት።”

2 ዜና መዋዕል 23:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 11:17, 18፤ 2ዜና 34:1, 31

2 ዜና መዋዕል 23:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቤተ መቅደስ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 10:27, 28
  • +ዘዳ 12:3፤ 2ዜና 34:1, 4
  • +ዘዳ 13:5፤ 1ነገ 18:40

2 ዜና መዋዕል 23:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በዳዊት እጅ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 29:38፤ ዘኁ 28:2
  • +1ዜና 23:6, 30, 31

2 ዜና መዋዕል 23:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 9:26፤ 26:1, 13

2 ዜና መዋዕል 23:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቤተ መንግሥት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 11:9
  • +2ነገ 11:19, 20
  • +1ነገ 7:7

ተዛማጅ ሐሳብ

2 ዜና 23:12ነገ 11:4
2 ዜና 23:22ዜና 8:14
2 ዜና 23:32ሳሙ 5:3
2 ዜና 23:32ሳሙ 7:8, 12፤ 1ነገ 2:4፤ 9:5፤ መዝ 89:20, 29
2 ዜና 23:41ዜና 24:3
2 ዜና 23:42ነገ 11:5-8፤ 1ዜና 9:22-25፤ 26:1
2 ዜና 23:51ነገ 7:1
2 ዜና 23:51ነገ 7:12
2 ዜና 23:61ዜና 23:28, 32
2 ዜና 23:82ነገ 11:9-12
2 ዜና 23:81ዜና 24:1፤ 26:1
2 ዜና 23:91ዜና 26:26, 27፤ 2ዜና 5:1
2 ዜና 23:92ሳሙ 8:7
2 ዜና 23:92ነገ 11:4
2 ዜና 23:112ነገ 11:2
2 ዜና 23:11ዘዳ 17:18
2 ዜና 23:111ሳሙ 10:1, 24
2 ዜና 23:122ነገ 11:13-16
2 ዜና 23:132ዜና 23:1
2 ዜና 23:131ነገ 1:39, 40
2 ዜና 23:162ነገ 11:17, 18፤ 2ዜና 34:1, 31
2 ዜና 23:172ነገ 10:27, 28
2 ዜና 23:17ዘዳ 12:3፤ 2ዜና 34:1, 4
2 ዜና 23:17ዘዳ 13:5፤ 1ነገ 18:40
2 ዜና 23:18ዘፀ 29:38፤ ዘኁ 28:2
2 ዜና 23:181ዜና 23:6, 30, 31
2 ዜና 23:191ዜና 9:26፤ 26:1, 13
2 ዜና 23:202ነገ 11:9
2 ዜና 23:202ነገ 11:19, 20
2 ዜና 23:201ነገ 7:7
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
2 ዜና መዋዕል 23:1-21

ሁለተኛ ዜና መዋዕል

23 በሰባተኛው ዓመት ካህኑ ዮዳሄ ድፍረት የተሞላበት እርምጃ በመውሰድ ከመቶ አለቆቹ+ ይኸውም ከየሮሃም ልጅ ከአዛርያስ፣ ከየሆሃናን ልጅ ከእስማኤል፣ ከኢዮቤድ ልጅ ከአዛርያስ፣ ከአዳያህ ልጅ ከማአሴያህ እና ከዚክሪ ልጅ ከኤሊሻፋጥ ጋር ስምምነት* አደረገ። 2 ከዚያም በይሁዳ ሁሉ በመዘዋወር ከመላው የይሁዳ ከተሞች ሌዋውያንንና+ የእስራኤልን የአባቶች ቤት መሪዎች ሰበሰቡ። ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጡ 3 መላው ጉባኤ በእውነተኛው አምላክ ቤት ከንጉሡ ጋር ቃል ኪዳን ገባ፤+ ከዚያም ዮዳሄ እንዲህ አላቸው፦

“እነሆ፣ ይሖዋ የዳዊትን ወንዶች ልጆች አስመልክቶ ቃል በገባው መሠረት የንጉሡ ልጅ ይገዛል።+ 4 እናንተም እንዲህ ታደርጋላችሁ፦ በሰንበት ቀን ተረኛ ከሚሆኑት ካህናትና ሌዋውያን+ መካከል አንድ ሦስተኛዎቹ በር ጠባቂዎች ይሆናሉ፤+ 5 አንድ ሦስተኛዎቹ ደግሞ በንጉሡ ቤት*+ ይሆናሉ፤ ሌላው አንድ ሦስተኛ በመሠረት በር ላይ ይሆናል፤ ሕዝቡ ሁሉ ደግሞ በይሖዋ ቤት ግቢዎች+ ውስጥ ይሆናል። 6 ከሚያገለግሉት ካህናትና ሌዋውያን በስተቀር ማንንም ወደ ይሖዋ ቤት እንዳታስገቡ።+ እነሱ የተቀደሱ ስለሆኑ ይግቡ፤ የቀረውም ሕዝብ ሁሉ ለይሖዋ ያለበትን ግዴታ ይፈጽማል። 7 ሌዋውያኑም እያንዳንዳቸው የጦር መሣሪያቸውን በእጃቸው ይዘው ንጉሡን ዙሪያውን ይክበቡት። ወደ ቤቱም ውስጥ የሚገባ ማንኛውም ሰው ይገደላል። ንጉሡ በሚሄድበት ሁሉ* አብራችሁት ሁኑ።”

8 ሌዋውያኑና የይሁዳ ሰዎች በሙሉ ልክ ካህኑ ዮዳሄ እንዳዘዛቸው አደረጉ። እያንዳንዳቸውም በሰንበት ቀን ተረኛ የሚሆኑትንና በሰንበት ቀን ከሥራ ነፃ የሚሆኑትን የራሳቸውን ሰዎች ወሰዱ፤+ ካህኑ ዮዳሄ ተራቸው ባይሆንም እንኳ በየምድቡ+ ያሉትን ከሥራ አላሰናበተም ነበርና። 9 ካህኑ ዮዳሄም በእውነተኛው አምላክ ቤት+ የነበሩትን የንጉሥ ዳዊት ጦሮች፣ ትናንሽ ጋሻዎችና* ክብ ጋሻዎች+ ለመቶ አለቆቹ+ ሰጣቸው። 10 ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ እያንዳንዳቸው የጦር መሣሪያቸውን* ይዘው በስተ ቀኝ በኩል ካለው የቤቱ ጎን አንስቶ በስተ ግራ በኩል እስካለው የቤቱ ጎን ድረስ በመሠዊያውና በቤቱ አጠገብ በንጉሡ ዙሪያ እንዲቆሙ አደረገ። 11 የንጉሡንም ልጅ+ አውጥተው አክሊሉን* ጫኑበት፤ ምሥክሩንም*+ ሰጡት፤ በዚህም መንገድ አነገሡት፤ ዮዳሄና ወንዶች ልጆቹም ቀቡት። ከዚያም “ንጉሡ ለዘላለም ይኑር!” አሉ።+

12 ጎቶልያ ሕዝቡ ሲሯሯጥና ንጉሡን ሲያወድስ ስትሰማ ወዲያውኑ በይሖዋ ቤት ወዳለው ሕዝብ መጣች።+ 13 ከዚያም ንጉሡ በመግቢያው ላይ ባለው በዓምዱ አጠገብ ቆሞ አየች። መኳንንቱና+ መለከት ነፊዎቹ ከንጉሡ ጋር ነበሩ፤ የምድሪቱም ሕዝብ ሁሉ እጅግ እየተደሰተና+ መለከት እየነፋ ነበር፤ የሙዚቃ መሣሪያ የያዙት ዘማሪዎችም ውዳሴውን ይመሩ* ነበር። በዚህ ጊዜ ጎቶልያ ልብሷን ቀዳ “ይህ ሴራ ነው! ሴራ ነው!” በማለት ጮኸች። 14 ካህኑ ዮዳሄ ግን በሠራዊቱ ላይ የተሾሙትን መቶ አለቆች ይዟቸው በመውጣት “ከረድፉ መካከል አውጧት፤ እሷን ተከትሎ የሚመጣ ሰው ካለ በሰይፍ ግደሉት!” አላቸው። ካህኑ “በይሖዋ ቤት ውስጥ እንዳትገድሏት” ብሎ ነበር። 15 በመሆኑም ያዟት፤ በንጉሡም ቤት* ወዳለው የፈረስ በር መግቢያ እንደደረሰች ገደሏት።

16 ከዚያም ዮዳሄ የይሖዋ ሕዝብ ሆነው እንዲቀጥሉ እሱ፣ ሕዝቡ ሁሉና ንጉሡ ቃል ኪዳን እንዲጋቡ አደረገ።+ 17 የምድሪቱም ሕዝብ ሁሉ ወደ ባአል ቤት* መጥቶ አፈራረሰው፤+ መሠዊያዎቹንና ምስሎቹንም ሰባበረ፤+ የባአል ካህን የነበረውን ማታንንም በመሠዊያዎቹ ፊት ገደሉት።+ 18 ከዚያም ዮዳሄ በይሖዋ ቤት የሚከናወኑትን ሥራዎች እንዲቆጣጠሩ ካህናቱንና ሌዋውያኑን ሾመ፤ እነሱም በሙሴ ሕግ ላይ በተጻፈው+ እንዲሁም ዳዊት ባዘዘው መሠረት* በደስታና በመዝሙር ለይሖዋ የሚቃጠል መሥዋዕት እንዲያቀርቡ ዳዊት በይሖዋ ቤት በየምድቡ የመደባቸው ናቸው።+ 19 በተጨማሪም በማንኛውም ነገር የረከሰ ሰው እንዳይገባ በር ጠባቂዎቹን+ በይሖዋ ቤት በሮች ላይ አቆመ። 20 ከዚያም መቶ አለቆቹን፣+ መኳንንቱን፣ የሕዝቡን ገዢዎችና የምድሪቱን ሕዝብ ሁሉ ሰበሰበ፤ ንጉሡንም አጅበው ከይሖዋ ቤት ወደ ታች አመጡት። በላይኛውም በር በኩል ወደ ንጉሡ ቤት* ገቡ፤ ንጉሡንም በመንግሥቱ+ ዙፋን+ ላይ አስቀመጡት። 21 በመሆኑም የምድሪቱ ሕዝብ ሁሉ እጅግ ተደሰተ፤ ጎቶልያንም በሰይፍ ስለገደሏት ከተማዋ ጸጥታ ሰፈነባት።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ