አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ ሕዝቅኤል የመጽሐፉ ይዘት ሕዝቅኤል የመጽሐፉ ይዘት 1 ሕዝቅኤል በባቢሎን ሆኖ የአምላክን ራእዮች ተመለከተ (1-3) የይሖዋ ሰማያዊ ሠረገላ ራእይ (4-28) አውሎ ነፋስ፣ ደመናና እሳት (4) አራት ሕያዋን ፍጥረታት (5-14) አራት መንኮራኩሮች (15-21) እንደ በረዶ የሚያብረቀርቅ ጠፈር (22-24) የይሖዋ ዙፋን (25-28) 2 ሕዝቅኤል የነቢይነት ተልእኮ ተሰጠው (1-10) “ቢሰሙም ባይሰሙም” (5) ሙሾ የተጻፈበት ጥቅልል አየ (9, 10) 3 ሕዝቅኤል አምላክ የሰጠውን ጥቅልል እንዲበላ ታዘዘ (1-15) ሕዝቅኤል ጠባቂ ሆኖ እንዲያገለግል ተሾመ (16-27) ቸልተኛ መሆን የደም ዕዳ ያስከትላል (18-21) 4 የኢየሩሳሌም ከበባ በምሳሌያዊ ሁኔታ ተገለጸ (1-17) በደሉን ለ390 ቀናትና ለ40 ቀናት ይሸከማል (4-7) 5 ኢየሩሳሌም ጥፋት እንደሚደርስባት በምሳሌያዊ ሁኔታ ተገለጸ (1-17) ነቢዩ ከተላጨ በኋላ ፀጉሩን ሦስት ቦታ ይከፍለዋል (1-4) ኢየሩሳሌም ከሌሎች ብሔራት የከፋ ድርጊት ፈጽማለች (7-9) በሦስት መንገድ ቅጣት ይደርስባታል (12) 6 በእስራኤል ተራሮች ላይ የተነገረ ትንቢት (1-14) አስጸያፊ የሆኑት ጣዖታት ውርደት ይከናነባሉ (4-6) ‘እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ’ (7) 7 ፍጻሜው ደርሷል (1-27) “በዓይነቱ ልዩ የሆነ ጥፋት” (5) “ብራቸውን በየጎዳናው ይጥላሉ” (19) ቤተ መቅደሱ ይረክሳል (22) 8 ሕዝቅኤል በራእይ ወደ ኢየሩሳሌም ተወሰደ (1-4) በቤተ መቅደሱ ውስጥ አስጸያፊ ነገሮች ታዩ (5-18) ሴቶች ለታሙዝ አለቀሱ (14) ወንዶች ፀሐይን አመለኩ (16) 9 ስድስት ፍርድ አስፈጻሚዎችና የጸሐፊ የቀለም ቀንድ የያዘ ሰው (1-11) ፍርድ ከመቅደሱ ይጀምራል (6) 10 ከመንኮራኩሮቹ መካከል እሳት ተወሰደ (1-8) የኪሩቦችና የመንኮራኩሮች መግለጫ (9-17) የአምላክ ክብር ከቤተ መቅደሱ ተነስቶ ሄደ (18-22) 11 ክፉዎቹ አለቆች ተወገዙ (1-13) ከተማዋ በድስት ተመሰለች (3-12) ተመልሰው እንደሚቋቋሙ ቃል ተገባላቸው (14-21) “አዲስ መንፈስ” ይሰጣቸዋል (19) የአምላክ ክብር ከኢየሩሳሌም ተነስቶ ሄደ (22, 23) ሕዝቅኤል በራእይ ወደ ከለዳውያን ምድር ተመለሰ (24, 25) 12 የስደት ጉዞው በምሳሌያዊ መንገድ ተገለጸ (1-20) የስደተኛ ጓዝ (1-7) አለቃው በጨለማ ይወጣል (8-16) የጭንቀት ምግብ፣ የፍርሃት ውኃ (17-20) አሳሳች የሆነው አባባል ውሸት መሆኑ ተረጋገጠ (21-28) “ከተናገርኩት ቃል ውስጥ የሚዘገይ አይኖርም” (28) 13 በሐሰተኞቹ ነቢያት ላይ የተነገረ ትንቢት (1-16) በኖራ የተለሰኑ ግድግዳዎች ይፈርሳሉ (10-12) በሐሰተኞቹ ሴት ነቢያት ላይ የተነገረ ቃል (17-23) 14 ጣዖት አምላኪዎች ተወገዙ (1-11) በኢየሩሳሌም ላይ ከሚወሰደው የፍርድ እርምጃ ማምለጥ አይቻልም (12-23) ጻድቅ የሆኑት ኖኅ፣ ዳንኤልና ኢዮብ (14, 20) 15 ኢየሩሳሌም፣ የማትጠቅም የወይን ተክል (1-8) 16 አምላክ ለኢየሩሳሌም ያለው ፍቅር (1-63) ተጥላ የተገኘች ልጅ (1-7) አምላክ አስዋባት፤ ከእሷም ጋር የጋብቻ ቃል ኪዳን ገባ (8-14) ታማኝ ሳትሆን ቀረች (15-34) በአመንዝራነቷ ተቀጣች (35-43) ከሰማርያና ከሰዶም ጋር ተነጻጸረች (44-58) አምላክ ቃል ኪዳኑን አስታወሰ (59-63) 17 የሁለቱ ንስሮችና የወይን ተክሉ እንቆቅልሽ (1-21) ለጋ የሆነው ቀንበጥ የሚያምር አርዘ ሊባኖስ ሆነ (22-24) 18 እያንዳንዱ በገዛ ኃጢአቱ ይጠየቃል (1-32) ኃጢአት የምትሠራ ነፍስ ትሞታለች (4) ልጅ በአባቱ ኃጢአት አይጠየቅም (19, 20) በክፉዎች ሞት ደስ አይሰኝም (23) ንስሐ መግባት ሕይወት ያስገኛል (27, 28) 19 ስለ እስራኤል አለቆች የተነገረ ሙሾ (1-14) 20 የእስራኤላውያን ዓመፅ (1-32) እስራኤላውያን ተመልሰው እንደሚቋቋሙ የተገባላቸው የተስፋ ቃል (33-44) በደቡብ ላይ የተነገረ ትንቢት (45-49) 21 የአምላክ የፍርድ ሰይፍ ተመዘዘ (1-17) የባቢሎን ንጉሥ በኢየሩሳሌም ላይ ጥቃት ይሰነዝራል (18-24) መጥፎው የእስራኤል አለቃ ከቦታው ይነሳል (25-27) ‘አክሊሉን አንሳ’ (26) “ሕጋዊ መብት ያለው እስኪመጣ ድረስ” (27) በአሞናውያን ላይ የተመዘዘ ሰይፍ (28-32) 22 ኢየሩሳሌም፣ የደም ዕዳ ያለባት ከተማ (1-16) እስራኤል ከላይ እንደሚሰፍ የማይረባ ቆሻሻ ናት (17-22) የእስራኤል ሕዝብና መሪዎች ተወገዙ (23-31) 23 ታማኝ ያልሆኑ ሁለት እህትማማቾች (1-49) ኦሆላ ከአሦር ጋር አመነዘረች (5-10) ኦሆሊባ ከባቢሎንና ከግብፅ ጋር አመነዘረች (11-35) በሁለቱ እህትማማቾች ላይ የተላለፈ የቅጣት ፍርድ (36-49) 24 እንደዛገ ድስት የሆነችው ኢየሩሳሌም (1-14) የሕዝቅኤል ሚስት ሞት እንደ ምልክት ሆኖ ያገለግላል (15-27) 25 በአሞን ላይ የተነገረ ትንቢት (1-7) በሞዓብ ላይ የተነገረ ትንቢት (8-11) በኤዶም ላይ የተነገረ ትንቢት (12-14) በፍልስጤም ላይ የተነገረ ትንቢት (15-17) 26 በጢሮስ ላይ የተነገረ ትንቢት (1-21) “የመረብ ማስጫ ቦታ” (5, 14) ድንጋዮቿና አፈሯ ወደ ባሕር ይጣላሉ (12) 27 ስለሰመጠው የጢሮስ መርከብ የተነገረ ሙሾ (1-36) 28 በጢሮስ ንጉሥ ላይ የተነገረ ትንቢት (1-10) “እኔ አምላክ ነኝ” (2, 9) ስለ ጢሮስ ንጉሥ የተነገረ ሙሾ (11-19) “በኤደን ነበርክ” (13) “የተቀባህ፣ የምትጋርድ ኪሩብ” (14) ‘ዓመፅ ተገኘብህ’ (15) በሲዶና ላይ የተነገረ ትንቢት (20-24) እስራኤል ተመልሳ ትቋቋማለች (25, 26) 29 በፈርዖን ላይ የተነገረ ትንቢት (1-16) ግብፅ ለባቢሎን ካሳ ሆና ትሰጣለች (17-21) 30 በግብፅ ላይ የተነገረ ትንቢት (1-19) ናቡከደነጾር ጥቃት እንደሚሰነዝር ትንቢት ተነገረ (10) የፈርዖን ክንድ ተሰበረ (20-26) 31 በግዙፍ አርዘ ሊባኖስ የተመሰለችው ግብፅ ትወድቃለች (1-18) 32 ስለ ፈርዖንና ስለ ግብፅ የተነገረ ሙሾ (1-16) ግብፅ ካልተገረዙት ጋር ትቀበራለች (17-32) 33 የጠባቂው ኃላፊነቶች (1-20) ኢየሩሳሌም መውደቋ ተነገረ (21, 22) በፍርስራሽ ውስጥ ለሚኖሩ የተላለፈ መልእክት (23-29) ሰዎች መልእክቱን ሰምተው በተግባር አያውሉትም (30-33) ሕዝቅኤል “የፍቅር ዘፈን” ሆነላቸው (32) “በመካከላቸው ነቢይ እንደነበረ ያውቃሉ” (33) 34 በእስራኤል እረኞች ላይ የተነገረ ትንቢት (1-10) ይሖዋ በጎቹን ይንከባከባል (11-31) ‘አገልጋዬ ዳዊት’ እረኛቸው ይሆናል (23) “የሰላም ቃል ኪዳን” (25) 35 በሴይር ተራሮች ላይ የተነገረ ትንቢት (1-15) 36 ስለ እስራኤል ተራሮች የተነገረ ትንቢት (1-15) የእስራኤል ተመልሶ መቋቋም (16-38) ‘ታላቅ ስሜን እቀድሰዋለሁ’ (23) “እንደ ኤደን የአትክልት ስፍራ” (35) 37 የደረቁ አጥንቶች የሞሉበት ሸለቆ ራእይ (1-14) አንድ ላይ የሚያያዙ ሁለት በትሮች (15-28) በአንድ ንጉሥ የሚመራ አንድ ብሔር (22) ዘላለማዊ የሰላም ቃል ኪዳን (26) 38 ጎግ በእስራኤል ላይ የሚሰነዝረው ጥቃት (1-16) በጎግ ላይ የሚነደው የይሖዋ ቁጣ (17-23) ‘ብሔራት እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ’ (23) 39 በጎግና በወታደሮቹ ላይ የሚደርስ ጥፋት (1-10) በሃሞን ጎግ ሸለቆ የሚፈጸም ቀብር (11-20) የእስራኤል መልሶ መቋቋም (21-29) የአምላክ መንፈስ በእስራኤል ላይ ይፈስሳል (29) 40 ሕዝቅኤል በራእይ ወደ እስራኤል ተወሰደ (1, 2) ሕዝቅኤል አንድ ቤተ መቅደስ በራእይ አየ (3, 4) ግቢዎቹና በሮቹ (5-47) በውጭ በኩል ያለው የምሥራቁ በር (6-16) ውጨኛው ግቢ፤ ሌሎች በሮች (17-26) የውስጠኛው ግቢና በሮች (27-37) የቤተ መቅደሱ አገልግሎት የሚከናወንባቸው ክፍሎች (38-46) መሠዊያው (47) የቤተ መቅደሱ በረንዳ (48, 49) 41 በቤተ መቅደሱ ውስጥ የሚገኘው መቅደስ (1-4) ግንቡና በጎን በኩል ያሉት ክፍሎች (5-11) በምዕራብ በኩል ያለው ሕንፃ (12) ሕንፃዎቹ ተለኩ (13-15ሀ) ውስጠኛው መቅደስ (15ለ-26) 42 የመመገቢያ ክፍሎቹ ሕንፃዎች (1-14) የቤተ መቅደሱ አራት ጎኖች ተለኩ (15-20) 43 የይሖዋ ክብር ቤተ መቅደሱን ሞላው (1-12) መሠዊያው (13-27) 44 የምሥራቁ በር እንደተዘጋ ይኖራል (1-3) የባዕድ አገር ሰዎችን በተመለከተ የወጡ ደንቦች (4-9) ሌዋውያንንና ካህናትን በተመለከተ የወጡ ደንቦች (10-31) 45 መዋጮ ሆኖ የተሰጠው ቅዱስ ስፍራና ከተማዋ (1-6) የአለቃው ድርሻ (7, 8) አለቆቹ በሐቀኝነት መሥራት ይጠበቅባቸዋል (9-12) የሕዝቡ መዋጮና አለቃው (13-25) 46 በተወሰኑ ወቅቶች የሚቀርቡ መባዎች (1-15) አለቃው ንብረቱን ውርስ አድርጎ ይሰጣል (16-18) መባዎች የሚቀቀሉባቸው ቦታዎች (19-24) 47 ከቤተ መቅደሱ የሚፈስ ጅረት (1-12) የውኃው ጥልቀት እየጨመረ ሄደ (2-5) የሙት ባሕር ውኃ ይፈወሳል (8-10) ረግረጋማ ቦታዎች አይፈወሱም (11) ለምግብነትና ለፈውስ የሚያገለግሉ ዛፎች (12) የምድሪቱ ወሰኖች (13-23) 48 ምድሪቱ ተከፋፍላ ተሰጠች (1-29) የከተማዋ 12 በሮች (30-35) “ይሖዋ በዚያ አለ” ተብላ የተጠራችው ከተማ (35)