ይህ ዓለም ከጥፋት ይተርፍ ይሆን?
ይህ አሳሳቢ ጥያቄ የይሖዋ ምሥክሮች ለሚያሰራጩት አንድ ትራክት የተሰጠ ርዕስ ነው። ባለፈው ዓመት አንድ በዋሽንግተን ዲ ሲ የሚኖር ሰው ይህ ትራክት ከደረሰው በኋላ ነገሩ በጣም እንዳሳሰበው ተናግሯል። እንዲህ ሲል ጻፈ:-
“በዚህች ዋና ከተማችን ለሚኖር ሰው ዓለም ወደ ፍጻሜዋ በመቅረብ ላይ መሆኗ በጣም ግልጽ ነው። ሰሜን አየርላንድ፣ የቀድሞዋ ዩጎዝላቭያ፣ የቀድሞዋ ሶቪየት ኅብረት ሪፓብሊኮች፣ ይህን የዛሬውን ዓለማችንን ለከበበውና ላጥለቀለቀው ጨለማና ጭንቀት በማስረጃነት ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው። የወህኒ ቤቶች መጣበብ፣ ሳንባ ነቀርሳና ጥቁሩ መቅሰፍት እንደ አዲስ ወረርሽኝ መስፋፋቱ በትራክታችሁ ውስጥ የገለጻችሁትን ቁምነገር እውነተኝነት የሚያረጋግጡ ናቸው።”
በመጨረሻም ሰውዬው “እባካችሁ፣ በዓይነቱ ብቸኛ ስለሆነው አመለካከታችሁ ተጨማሪ ማብራሪያ ላኩልኝ። በተጨማሪም ያለ ክፍያ የምታስተምሩትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ጀምሩልኝ” ብሏል።
የይሖዋ ምሥክሮች መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሰው ልጆች የወደፊት ሁኔታ የሚናገረውን ለሰዎች ያሳውቃሉ። ከላይ የተጠቀሰው ትራክት እንዲላክልዎ ወይም መጽሐፍ ቅዱስን ያለ ክፍያ ለመማር የሚፈልጉ ከሆነ የይሖዋ ምሥክሮች፣ ፖ.ሣ.ቁ. 5522፣ አዲስ አበባ ብለው ወይም በገጽ 5 ላይ ካሉት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው ይጻፉ።