መጽሐፍ ቅዱስ ምን መልስ ይኖረው ይሆን ብለው ራስዎን ጠይቀው ያውቃሉን?
እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን በራሱ ላይ አፈሰሰ ማለት ነውን?
“ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፣ እነሆም ሰማያት ተከፈቱ፣ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፤ እነሆም ድምፅ ከሰማያት መጥቶ:- በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ።”— ማቴዎስ 3:16, 17
የሚከተሉት በገጽ 25 ላይ ለተጠየቁት ጥያቄዎች መልስ ከሚሰጡ ጥቅሶች ጥቂቶቹ ናቸው:-
1. ዘ ኢንሳይክሎፔድያ ኦቭ ሪልጅን “በአሁኑ ጊዜ የሥላሴ መሠረተ ትምህርት በዕብራይስጡ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደማይገኝ ሃይማኖታዊ ሊቃውንት ይስማማሉ” ይላል። በተጨማሪም ዘ ኒው ካቶሊክ ኢንሳይክሎፔድያ “ብሉይ ኪዳን የቅድስት ሥላሴን መሠረተ ትምህርት አያስተምርም” ይላል።
2. “እስራኤል ሆይ፣ ስማ፤ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው።” (ዘዳግም 6:4) “እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ላይ ይነግሣል፤ በዚያ ቀን እግዚአብሔር አንድ፣ ስሙም አንድ ይሆናል።”— ዘካርያስ 14:9
3. “የእግዚአብሔርም መንፈስ [በሳምሶን ላይ] በኃይል ወረደበት፤ ክንዱም የታሰረበት ገመድ በእሳት እንደተበላ እንደ ተልባ እግር ፈትል ሆነ፣ ማሰሪያዎቹም ከእጁ ወደቁ።” (መሳፍንት 15:14) “ለዘሩባቤል የተባለው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው:- በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፣ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።”— ዘካርያስ 4:6
4. “የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ በኃይል ወረደ፤ ጠቦትን እንደሚቆራርጥ በእጁ ምንም ሳይኖር ቆራረጠው።” (መሳፍንት 14:6) “መንፈሴን በዘርህ ላይ በረከቴንም በልጆችህ ላይ አፈስሳለሁ።”— ኢሳይያስ 44:3
5. “ስለዚህ እወቅ፣ አስተውልም፤ ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ትእዛዙ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ አለቃው እስከ መሢሕ ድረስ ሰባት ሱባዔና ስድሳ ሁለት ሱባዔ ይሆናል። . . . ከስድሳ ሁለት ጊዜ ሰባትም በኋላ መሢሕ ይገደላል፣ በእርሱም ዘንድ ምንም የለም።”— ዳንኤል 9:25, 26
6. “ሰማያትን የፈጠረ እግዚአብሔር፣ እርሱም ምድርን የሠራና ያደረገ ያጸናትም፣ መኖሪያም ልትሆን እንጂ ለከንቱ እንድትሆን ያልፈጠራት አምላክ፤ እንዲህ ይላል:- እኔ እግዚአብሔር [“ይሖዋ” አዓት ] ነኝ ከእኔም በቀር ሌላ የለም።”— ኢሳይያስ 45:18
7. “እኔ አምላክ ነኝና፣ ሌላም የለምና የቀድሞውን የጥንቱን ነገር አስቡ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ እንደ እኔም ያለ ማንም የለም።”— ኢሳይያስ 46:9
8. “እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤ እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴም ቅን ነው፣ የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና።” (ዮሐንስ 5:30) “የምትወዱኝስ ብትሆኑ ከእኔ አብ ይበልጣልና ወደ አብ በመሄዴ ደስ ባላችሁ ነበር።”— ዮሐንስ 14:28
9. “እኔንም ታውቁኛላችሁ ከወዴትም እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ፤ እኔም በራሴ አልመጣሁም ነገር ግን እናንተ የማታውቁት የላከኝ እውነ ተኛ ነው፤ እኔ ግን ከእርሱ ዘንድ ነኝ፣ እርሱም ልኮኛልና አውቀዋለሁ።”— ዮሐንስ 7:28, 29
10. “መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው።” (ዮሐንስ 1:18) “አብን ያየ ማንም የለም፣ ከእግዚአብሔር ከሆነ በቀር፣ እርሱ አብን አይቶአል።”— ዮሐንስ 6:46
11. “የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ስላልሁ እናንተ አብ የቀደሰውን ወደ ዓለምም የላከውን:- ትሳደባለህ ትሉታላችሁን?”— ዮሐንስ 10:36
12. “የምትወዱኝስ ብትሆኑ ከእኔ አብ ይበልጣልና ወደ አብ በመሄዴ ደስ ባላችሁ ነበር።”— ዮሐንስ 14:28
13. “ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም።” (ማቴዎስ 24:36) “ሁሉም [የኢየሱስ ተከታዮች] አንድ ይሆኑ ዘንድ፣ ከቃላቸው የተነሣ በእኔ ስለሚያምኑ ደግም እንጂ ስለ እነዚህ ብቻ አልለምንም፤ አንተ እንደ ላክኸኝ ዓለም ያምን ዘንድ፣ አንተ፣ አባት ሆይ፣ በእኔ እንዳለህ እኔም በአንተ፣ እነርሱ ደግሞ በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ እለምናለሁ።”— ዮሐንስ 17:21
14. “እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ።” (ዮሐንስ 1:29) “አንተ ክርስቶስ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆንህ አምነናል አውቀናልም።”— ዮሐንስ 6:69
15. “ከደመናውም:- የምወደው ልጄ ይህ ነው፣ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።”— ማርቆስ 9:7
16. “መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ።” (ሥራ 1:8) “እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው።”—ሥራ 10:38
17. በስተግራ ያለውን ሥዕልና በገጽ 26 ላይ ከላይ ያለውን ጽሑፍ ተመልከት
18. “የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፣ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።”— ዕብራውያን 12:2
19. “በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፣ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው።”— ፊልጵስዩስ 2:9
20. “ነገር ግን የወንድ ሁሉ ራስ ክርስቶስ፣ የሴትም ራስ ወንድ፣ የክርስቶስም ራስ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ልታውቁ እወዳለሁ።”— 1 ቆሮንቶስ 11:3
21. “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፣ . . . በሰማይና በምድርም እንደ ሥራህ እንደ ኃይልህም ይሠራ ዘንድ የሚችል አምላክ ማን ነው?” (ዘዳግም 3:24) “[ኢየሱስ] ሁሉ ከተገዛለት በኋላ ግን እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉ ይሆን ዘንድ በዚያን ጊዜ ልጁ ራሱ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት ይገዛል።”— 1 ቆሮንቶስ 15:28
[በገጽ 40 ላይ የሚገኝ የተቀነጨበ ሐሳብ]
እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን በራሱ ላይ አፈሰሰ ማለት ነውን?