“እናንተ በመኖራችሁ አመስጋኝ ነኝ”
እነዚህ ቃላት ኖርዝ ካሮላይና፣ ዩ ኤስ ኤ ውስጥ የሚኖር አንድ ሰው ብሩክሊን ኒው ዮርክ ለሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች ዋና መሥሪያ ቤት ከጻፈው ደብዳቤ የተወሰዱ ናቸው። በተጨማሪም ሰውዬው እንዲህ ብሎ ነበር:- “በንቁ! መጽሔት ላይ ባቀረባችሁት ግብዣ መሠረት የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እፈልጋለሁ፤ እንዲሁም ሲኦልን በተመለከተ የቻላችሁትን ያህል ማንኛውንም ዓይነት ማብራሪያ ብትሰጡኝ ደስ ይለኛል። . . .
“የባፕቲስት ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታይ ሆኜ ያደግኩ ቢሆንም ገና ከልጅነቴ ጀምሮ አንዳንድ የማልስማማባቸው ሃይማኖታዊ ትምህርቶች ነበሩ።
“ከ1965 ጀምሮ ጽሑፎቻችሁን ሳነብብ ቆይቻለሁ። የማነብበው ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር እያገናዘብኩ ሲሆን ጽሑፎቻችሁ ውስጥ የሰፈረው በጠቅላላ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይስማማል። ስለ አምላክና ስለ ኢየሱስ እውነቱን ለማወቅ ዘወትር እመኝ ነበር፤ አሁን በጽሑፎቻችሁና በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት ለጥያቄዎቼ ትክክለኛ መልስ እያገኘሁ ነው ለማለት እችላለሁ።”
እርስዎም ቢሆኑ የይሖዋ ምሥክሮች የሚያቀርቡትን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ትምህርቶች ያደንቁ ይሆናል። የይሖዋ ምሥክሮች ምን ብለው ያምናሉ? የተባለውን ትራክት ለማግኘት ወይም ያለ ክፍያ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዲደረግልዎ የሚፈልጉ ከሆነ የይሖዋ ምሥክሮች የፖ. ሣ. ቁ. 5522፣ አዲስ አበባ በማለት ወይም ገጽ 5 ላይ ከተዘረዘሩት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው ይጻፉ።