የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g97 1/8 ገጽ 32
  • ፕላኔቷ ምድራችን ግሩም ጊዜ ይጠብቃታል

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ፕላኔቷ ምድራችን ግሩም ጊዜ ይጠብቃታል
  • ንቁ!—1997
ንቁ!—1997
g97 1/8 ገጽ 32

ፕላኔቷ ምድራችን ግሩም ጊዜ ይጠብቃታል

“በአሁኑ ጊዜ የምድር ሙቀት ከ600 ዓመታት ወዲህ ታይቶ በማይታወቅ መጠን እንደጨመረ የተደረጉ ጥናቶች ይጠቁማሉ” ሲል በቶሮንቶ እየታተመ የሚወጣው ግሎብ ኤንድ ሜይል የተባለ መጽሔት ዘግቧል። በ1995 በማዕከላዊ ዩናይትድ ስቴትስ የተከሰተው ከፍተኛ የሙቀት መጠን ቺጋጎ ውስጥ ከ500 በላይ ሰዎችን ገድሏል። በሕንድና በአውስትራሊያ ተመሳሳይ የሆነ ከፍተኛ የሙቀት መጠን የተከሰተ ሲሆን እንግሊዝ “ካለፉት 200 ዓመታት ወዲህ ለሦስተኛ ጊዜ ከፍተኛ ድርቅ ያጠቃበት በጋ” አጋጥሟታል።

የዚህ መንስኤ ምንድን ነው? በካናዳ የፌዴራሉ የአካባቢ ጥናት ዲፓርትመንት የአየር ንብረት ኤክስፐርት የሆኑት ሄንሪ ሄንጄቬልድ “የሰው ልጅ በዓለም የአየር ንብረት ላይ መጥፎ ተጽዕኖ እንዳሳደረ ማስረጃው በአመዛኙ ያሳያል” ብለዋል። ግሎብ ኤንድ ሜይል የተባለው መጽሔት እንደዘገበው ከሆነ “አሁን የሚታየው ያልተለመደ የአየር ጠባይ የዓለም የሙቀት መጠን መጨመር የሚያስከትላቸውን ውጤቶች ለማወቅ በኮምፒዩተር ላይ ከተደረጉት ጥናቶች ጋር አንድ ዓይነት ሲሆን ይህ ችግር በአብዛኛው በነዳጅ ዘይት መቃጠል ምክንያት የተከሰተ ነው የሚል ግምት አሳድሯል።”

በመላው ዓለም የሙቀት መጠን ጨምሯል የሚለው ሐሳብ አሁንም በሳይንቲስቶች ዘንድ እያወዛገበ ነው። ሆኖም ዘ ኒው ኢንሳይክሎፔድያ ብሪታኒካ “የሰው ልጅ የከባቢውን አየር ጠባይ ለመረዳት ከሚወስድበት ጊዜ ይልቅ እየፈጸመበት ያለው ብክለት ፈጣን ነው” የሚል አስተያየት ሰንዝሯል።

ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ምድር “ለዘላለም ነው” ብሎ ስለሚናገር ደስ ሊለን ይገባል። (መክብብ 1:4) ይህ የሆነው ፈጣሪያችን ይሖዋ አምላክ ሰውም ሆነ ማናቸውም የተፈጥሮ ኃይል ምድርን እንዲያጠፋት ስለማይፈቅድ ነው። ከዚህ በተቃራኒ አምላክ ‘ምድርን የሚያጠፏትን ያጠፋል።’— ራእይ 11:17, 18

በተጨማሪም ይሖዋ አምላክ ለፕላኔቷ ምድራችንና ለታዛዥ የሰው ልጆች በሙሉ ወደፊት ግሩም የሆነ ጊዜ እንደሚያመጣላቸው መጽሐፍ ቅዱስ ያረጋግጥልናል። “ገሮች ምድርን ይወርሳሉ፣ በብዙም ሰላም ደስ ይላቸዋል።” የምድር የወደፊት ዕጣ በሰው ልጆች እጅ ሳይሆን በአምላክ እጅ መሆኑ እንዴት ያስደስታል!— መዝሙር 37:11፤ 72:16፤ ኢሳይያስ 65:17-25፤ 2 ጴጥሮስ 3:13

ወደፊት የሚወጡትን የንቁ! መጽሔት እትሞች ለማግኘት ከፈለጉ በአካባቢዎ የሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮችን ማነጋገር ይችላሉ ወይም በገጽ 5 ላይ ካሉት አድራሻዎች አመቺ ወደ ሆነው ይጻፉ።

[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

NASA photo

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ