የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g97 7/8 ገጽ 12
  • ኤሚ ዜደን መንገድ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ኤሚ ዜደን መንገድ
  • ንቁ!—1997
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በናዚ አገዛዝ ወቅት የይሖዋ ምሥክሮች ምን ደርሶባቸዋል?
    ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ብዙ ጊዜ የሚነሱ ጥያቄዎች
  • እንደ ጴጥሮስ መጽናት ትችላላችሁ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2023
  • ክፍል 3—በዕገዳ ሥር በነበርንባቸው ዓመታት ይሖዋ እንክብካቤ አድርጐልናል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • ሠራተኞች የጥቃት ዒላማ የሚሆኑት እንዴት ነው?
    ንቁ!—2004
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—1997
g97 7/8 ገጽ 12

ኤሚ ዜደን መንገድ

ከስሙ በስተጀርባ ያለው ታሪክ

ግንቦት 1992 በጀርመን፣ በበርሊን ከተማ የሚገኝ አንድ መንገድ ኤሚ ዜደን በምትባል አንዲት የይሖዋ ምሥክር ስም ተሰየመ።

ኤሚ የተወለደችው በ1900 ነው። ሪቻርድ ዜደን የተባለ አንድ አይሁዳዊ ነጋዴ አግብታ የነበረ ሲሆን ባሏ በናዚ የአገዛዝ ዘመን ኦሽቪትዝ በሚባለው ማጎሪያ ካምፕ ውስጥ ሞቷል። ሪቻርድ እና ኤሚ፣ ሆርስት ሽሚት የሚባል ጉዲፈቻ ልጅ ነበራቸው። ሆርስት እና ሌሎች ሁለት ወጣት የይሖዋ ምሥክሮች ለውትድርና አገልግሎት በተጠሩ ጊዜ መደበቅ ግድ ሆነባቸው።

ኤሚ ለሆርስትና ለሁለት ጓደኞቹ መደበቂያ ቦታ አዘጋጀችላቸው። ሆኖም ውሎ አድሮ ያሉበት ቦታ ታወቀና ተያዙ። ሦስቱ ልጆች በውትድርና አገልግሎት ለመካፈል ፈቃደኛ ባለመሆናቸውና ኤሚ ደግሞ እነርሱን በመደበቋ ምክንያት አራቱም ሞት ተፈረደባቸው። ሁለቱ የሆርስት ጓደኞች አንገታቸው ተቆረጠ። ኤሚ ይግባኝ ብትጠይቅም ተቀባይነት ሳታገኝ ቀረች። እርሷም ሰኔ 9, 1944 በበርሊን ከተማ በሚገኘው በፕሉትሰንዜ አንገቷ ተቆረጠ።a ሆርስት ሽሚት ከናዚ ስደት ተረፈ፤ ከጊዜ በኋላ ደግሞ ከማጎሪያ ካምፕ በሕይወት የተረፈች አንዲት የይሖዋ ምሥክር አገባ።

ግንቦት 7, 1992 በበርሊን የሚገኝ አንድ መንገድ ኤሚ ዜደን ተብሎ ተሰየመ። አንድ የጀርመን ባለ ሥልጣን ባቀረቡት ንግግር ላይ ኤሚ ያሳየችው ድፍረት የሚደነቅ እንደሆነ ገልጸው ‘ከተረሱት በርካታ የጦርነቱ ሰለባዎች’ እንደ ምሳሌ አድርገው ጠቅሰዋታል።

[የግርጌ ማስታወሻ]

a በበርሊን-ፕሉትሰንዜ መታሰቢያ የሚገኙት የመንግሥት ሰነዶች እንደሚገልጹት ኤሚ ዜደን የተገደለችው ሰኔ 9, 1944 ነው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ