መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትራክቶች የሚያስገኙት ውጤት
በሩሲያ በሞስኮ አቅራቢያ በምትገኘው በጎሊሲኖ ከተማ አንድ የይሖዋ ምሥክር፣ ሕፃን ልጅዋን በጋሪ ላይ አስቀምጣ ለምትገፋ አንዲት ሴት በቤተሰብ ኑሮ ተደሰት የሚል ርዕስ ያለውን ትራክት ሰጣት። ከዚያም ምሥክሩ መንገዱን ቀጠለ። ይሁን እንጂ ወዲያውኑ ሴትየዋ ስትጠራው ይሰማል። እርሱ ላይ ለመድረስ ሕፃን ልጅዋ የተቀመጠበትን ጋሪ እየገፋች ትሮጥ ነበር።
ሴትየዋ ተጨማሪ እውቀት ለማግኘት እንደምትፈልግ ስትነግረው ሌሎች ሁለት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ርዕስ ያላቸው ትራክቶች ሰጣት። በተጨማሪም ከእርሱ ጋር ለመገናኘት እንድትችል የስልክ ቁጥሩን ሰጣት። በዚያኑ ዕለት ምሽት ደወለችለትና በየሳምንቱ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዲደረግላት ዝግጅት አደረጉ። በሰባት ወራት ጊዜ ውስጥ እርሷና እህቷ ራሳቸውን ለአምላክ ወስነው ተጠመቁ።
እርስዎም በቤተሰብ ኑሮ ተደሰት፣ ለተጨነቁ ሰዎች የሚሆን መጽናኛ፣ ዓለምን የሚገዛው ማን ነው? እንዲሁም ሰላም በሰፈነበት አዲስ ዓለም ውስጥ የሚገኝ ሕይወት የሚሉትን ትራክቶች ለማንበብ የሚፈልጉ ከሆነ የይሖዋ ምሥክሮች የፖ. ሣ. ቁ. 5522፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ብለው አሊያም በገጽ ሁለት ላይ ከተዘረዘሩት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው ይጻፉ።