የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g98 12/8 ገጽ 32
  • መልሶቹን ማግኘት የምንችለው ከየት ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መልሶቹን ማግኘት የምንችለው ከየት ነው?
  • ንቁ!—1998
ንቁ!—1998
g98 12/8 ገጽ 32

መልሶቹን ማግኘት የምንችለው ከየት ነው?

ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥራቸው እየጨመረ የመጣ በርካታ ሰዎች በዛሬው ጊዜ በሚገጥሟቸው ችግሮችና ውስብስብ የሆኑ ጥያቄዎች ተውጠዋል። መዋሸትን በተመለከተ ምን ዓይነት አመለካከት ሊኖረን ይገባል? ቁማር መጫወት ተገቢ ነው? በመናፍስት አምልኮ መካፈልን በሚመለከት ምን ለማለት ይቻላል? ጽንስ ማስወረድን በተመለከተ ምን ዓይነት አመለካከት ሊኖረን ይገባል? መስከር ወይም ያላገቡ ሰዎች የፆታ ግንኙነት መፈጸማቸው ስህተት ነውን?

ጥያቄዎቹ ማብቂያ የላቸውም። እንዲሁም በእኛ ሕይወት ላይ ብቻ ሳይሆን በምንወዳቸው ሰዎች ሕይወት ላይም ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራሉ። ሰዎች ሕይወታቸውን በተሻለ መንገድ ለመምራት የሚያስችሉ መልሶች ማግኘት ይፈልጋሉ። እንደነዚህ ካሉት ሰዎች መካከል አንዷ የሆነችው በሚሲሲፒ፣ ዩናይትድ ስቴትስ የምትኖር ሴት ለመጠበቂያ ግንብ ማኅበር የሚከተለውን ጽፋለች:-

“ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? በተባለው መጽሐፋችሁ የመጨረሻ ገጽ ላይ ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ወይም ነፃ የሆነ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዲደረግልኝ እፈልግ እንደሆነ የሚጠይቅ ጽሑፍ አነበብኩ። አዎን፣ እፈልጋለሁ!

“ከ1995 የበጋ ወራት ጀምሮ መጽሐፍ ቅዱሴን በማንበብና በማጥናት ላይ ነኝ። የራሴን መንፈሳዊነት ለማሳደግና ሌሎች ሰዎችን ለማስተማር በሚያስችል ደረጃ መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት የቻልኩትን ሁሉ ጥረት አደርጋለሁ። እንዳላችሁት ተጨማሪ መረጃ የምትልኩልኝ ከሆነ ለመቀበል ፈቃደኛ ነኝ!”

እርስዎም ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? የተባለውን ባለ 192 ገጽ መጽሐፍ ለማግኘት ወይም አንድ ሰው እቤትዎ መጥቶ መጽሐፍ ቅዱስን ያለ ክፍያ እንዲያስጠናዎት የሚፈልጉ ከሆነ የይሖዋ ምሥክሮች፣ ፖ. ሣ. ቁ. 5522፣ አዲስ አበባ ብለው ወይም በገጽ 5 ላይ ካሉት አድራሻዎች አመቺ ወደ ሆነው ይጻፉ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ