“ንቁ! ፍጹም ተስማሚ ሆኖ አግኝቼዋለሁ”
ከላይ የተጠቀሰውን አስተያየት የሰጠው በአፍሪካዊቷ አገር በናይጄሪያ፣ ቤኒን ሲቲ ውስጥ የሚኖር አንድ የ16 ዓመት ሙስሊም ወጣት ነው። በናይጄሪያ ለሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች ቅርንጫፍ ቢሮ በጻፈው ደብዳቤ ላይ እንዲህ ሲል ገልጿል:-
“በአንድ ጓደኛዬ ቤት ንቁ! መጽሔቶች አገኘሁና ዘጠኙን ተውሼ ወሰድኩ። ሁሉንም በአንድ ቀን ከዳር እስከ ዳር አነበብኳቸው! ይህን ደብዳቤ የጻፍኩት ይሖዋን ጨምሮ ይህን ግሩም መጽሔት ያዘጋጁትን ሁሉ ለማመስገን ነው! በተለይ ደግሞ አካባቢያዊ ጉዳዮችን ከመጽሐፍ ቅዱስና ከአምላክ ጋር ያያያዛችሁበት መንገድ በጣም አስደንቆኛል። የናይጄሪያ የአካባቢ ጥበቃ ድርጅት አባል እንደ መሆኔ መጠን ስለ አካባቢ/ተፈጥሮ የሚገልጹ ጽሑፎች በማሰባሰብ ላይ ነበርኩ። እናም ንቁ! ፍጹም ተስማሚ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። እባካችሁ በወር ሁለት ጊዜ እየታተመ የሚወጣውን ይህን የንቁ! መጽሔት እንዴት ማግኘት እንደምችል ግለጹልኝ።”
ይህን ቅጂ ከማግኘትዎ በፊት የንቁ! መጽሔት አንብበው አያውቁ ይሆናል። ሌላ ቅጂ ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ የይሖዋ ምሥክሮች፣ ፖ.ሣ.ቁ. 5522፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ብለው ወይም በገጽ 5 ላይ ከተዘረዘሩት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው በመጻፍ መጽሔቱ እንዲላክልዎ መጠየቅ ይችላሉ። ሌላ ቅጂ ልንልክልዎት እንችላለን፤ አለዚያም በጥያቄዎ መሠረት አንድ ሰው እቤትዎ ድረስ መጥቶ የምንኖርበት ዘመን ስላለው ትርጉም ሊያወያይዎት ይችላል።
□ በቅርቡ የወጣ የንቁ! መጽሔት ማግኘት እፈልጋለሁ።
□ ያለ ክፍያ የሚደረገውን የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በተመለከተ እንድታነጋግሩኝ እፈልጋለሁ።
[ምንጭ]
ሉል:-Courtesy of Replogle Globes, Inc.