ለጥያቄዎቹ መልስ አገኘ
በዓለም ዙሪያ ያሉ በርካታ ሰዎች ኑሮ ሊወጡት ያልቻሉት ጋራ ሆኖባቸዋል። አንዳንዶች ይህ የሆነበትን ምክንያት ለማወቅ ሲጥሩ ይታያል። በግሮድኖ፣ ቤላሩስ የሚኖር ሁለት ልጆች ያሉት አንድ የ35 ዓመት ጎልማሳ የሚከተለውን ደብዳቤ ጽፏል:-
“በመንገድ ላይ ስሄድ አንዲት ሴት አስቆመችኝና ንቁ! መጽሔት አበረከተችልኝ። ለጊዜው መጽሔቱ ስለምን እንደሚናገር አላወቅኩም ነበር። ሆኖም ማራኪ ስለነበር ወሰድኩት። እቤት ገብቼ በመጽሔቱ ላይ ያሉትን ርዕሶች ስመለከት ፍላጎቴን ቀሰቀሱት።
“በእርግጥ እኔ ሃይማኖተኛ ነኝ ማለት አልችልም። ይሁን እንጂ ይረብሹኝ ለነበሩት በርካታ ጥያቄዎች አሳማኝ የሆኑ መልሶች ከጽሑፋችሁ ለማግኘት ችያለሁ። በአሁኑ ጊዜ ያለው ኑሮ ቀላል አይደለም። የመጽሐፍ ቅዱስ እርዳታ በእጅጉ ያስፈልገናል። ስለ አምላክና ስለ ትምህርቶቹ ተጨማሪ ማብራሪያ የሚሰጡ ጽሑፎች ብትልኩልኝ ደስ ይለኛል። ለረዥም ጊዜያት በአእምሮዬ ውስጥ ይጉላሉ ለነበሩ በርካታ ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ጥረት ሳደርግ ቆይቻለሁ። በዚህ ረገድ ጽሑፋችሁ በጣም ጠቅሞኛል።”
የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው?—እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ? የተባለው ባለ 32 ገጽ ብሮሹር በሚልዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች ጠቃሚ የሆነ እርዳታ አበርክቷል። ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ አለዚያም ደግሞ በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው በመላክ ይህን ብሮሹር ማግኘት ይችላሉ።
□ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው?—እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ? የተባለውን ብሮሹር ላኩልኝ።
□ መጽሐፍ ቅዱስ መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።