የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g99 12/8 ገጽ 32
  • “ፈጽሞ አልቆጭም”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ፈጽሞ አልቆጭም”
  • ንቁ!—1999
ንቁ!—1999
g99 12/8 ገጽ 32

“ፈጽሞ አልቆጭም”

“ጋዜጦችን፣ ልብ ወለዶችንና ግጥሞችን ማንበብ እወዳለሁ፤ ሆኖም ንቁ! የማንበብ ፍላጎት ፈጽሞ አልነበረኝም” ሲል በሰሜናዊ ብራዚል የሚኖር አንድ ሰው ጽፏል። “የይሖዋ ምሥክሮች ወደ ቤት ሲመጡ ካየሁ የትንሿን አፓርታማዬን በር ዘግቼ እቤት የሌለሁ ለማስመሰል ድምፄን አጠፋ ነበር። ካነጋገርኳቸው ደግሞ በተቻለ መጠን ቶሎ ብዬ መጽሔቶቹን እቀበላቸውና ሳላነባቸው አስቀምጣቸው ነበር።

“አንድ ቀን ምንም የማነበው ነገር ስላልነበረኝ ሽፋኑ ላይ ‘ከአጭበርባሪዎች ተጠበቁ!’ የሚል ርዕስ ያለውን የመስከረም 22, 1997 ንቁ! (እንግሊዝኛ) አንስቼ ማንበብ ጀመርኩ። የትምህርቶቹና የመረጃዎቹ ግልጽ የሆነ አቀራረብ ስሜቴን ማረከው። ወዲያውኑ ቀደም ሲል የወሰድኳቸውንና በየስርቻው ያስቀመጥኳቸውን ቅጂዎች በሙሉ መፈለግ ጀመርኩ። ከዚያም ከአንድ የይሖዋ ምሥክር ጋር ተገናኘሁና የንቁ! ኮንትራት ገባሁ። አሁን መጽሔቱን መውሰድና ማንበብ ከጀመርኩ ስምንት ወራት ያለፉ ሲሆን ይህን በማድረጌ ፈጽሞ አልቆጭም።”

እርስዎም ሊገምቱት እንደሚችሉት የይሖዋ ምሥክሮች ብዙ ሰዎችን በሚያሳስቧቸው ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ ሌሎች ጽሑፎችንም ያወጣሉ። ብዙ ሰዎች “አምላክ በእርግጥ ለሰው ልጆች ያስባልን? የሚያስብ ከሆነ መከራ እንዲኖር ለምን ፈቀደ? መከራ የሚያበቃበት ጊዜ ይመጣ ይሆን?” እያሉ ይጠይቃሉ። አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን? የተባለው ባለ 32 ገጽ ብሮሹር ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል። ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ አለዚያም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው በመላክ የዚህን ብሮሹር ቅጂ ማግኘት ይችላሉ።

□ አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን? የተባለውን ብሮሹር ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስ መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ