የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g01 11/8 ገጽ 32
  • በትራክቱ ተማረከ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በትራክቱ ተማረከ
  • ንቁ!—2001
ንቁ!—2001
g01 11/8 ገጽ 32

በትራክቱ ተማረከ

አንድ ወጣት በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፑብሊክ በባንጉዊ ከተማ አውራ ጎዳና ሲጓዝ ዓለምን የሚገዛው ማን ነው? የተሰኘው ትራክት ይደርሰዋል። ጥያቄው ቀልቡን ስለሳበው ስለ ጉዳዩ የበለጠ ለማወቅ ጓጉቶ ነበር። ትራክቱን ማንበብ ሲጀምር ጓደኛውም እንደርሱ ፍላጎት አደረበት። ሆኖም የነበረው አንድ ቅጂ ብቻ ስለሆነ የትራክቷ ባለቤት ሊሰጠው አልፈለገም። ምን መላ ይፈጥሩ ይሆን?

መፍትሔ ሆኖ ያገኙት 100 CFA (በኢትዮጵያ ብር 1.31 ገደማ) ከፍሎ ትራክቷን ፎቶ ኮፒ ማስነሣት ነበር። በባንጉዊ ለሚኖር ተማሪ ይህ ብዙ ገንዘብ ነው። ሆኖም በዓለም ዙሪያ የሚኖሩ በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የደረሳቸውን መልእክት እነሱም በማግኘታቸው ተደስተው ነበር።

እርስዎም የዓለም አገዛዝ በቅርቡ ተለውጦ የተሻለ የሚሆነው እንዴት እንደሆነ ለማንበብ ከፈለጉ የዚህን ትራክት ቅጂ እንዲያገኙ እንጋብዝዎታለን። ይህንን ትራክት እና “እነሆ፣ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ” የተባለውን ባለ 32 ገጽ ብሮሹር አንድ ቅጂ ለማግኘት ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ካሉት አድራሻዎች ተስማሚ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

□ ዓለምን የሚገዛው ማን ነው? የተሰኘውን ትራክትና “እነሆ፣ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ ” የተሰኘውን ብሮሹር ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ