“ተማሪዎች ምርምር ለማድረግ አዘውትረው ይጠቀሙበታል”
ሚና ዤራይስ በምትባለው የብራዚል ግዛት በዲቪኖፖሊስ የሚኖር አንድ ዐቃቤ መጻሕፍት ተማሪዎች በንቁ! መጽሔት በእጅጉ መማረካቸውን አስመልክቶ በብራዚል ለሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች ቢሮ እንዲህ ሲል ጻፈ:-
“የምሠራበት የማዘጋጃ ቤት ቤተ መጻሕፍት [በይሖዋ ምሥክሮች] የታተሙ መጻሕፍትንና መጽሔቶችን አልፎ አልፎ በእርዳታ መልክ ያገኛል። ምንም እንኳን እዚህ ካሉት ተማሪዎች መካከል አንዳቸውም የይሖዋ ምሥክር ባይሆኑም በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ምርምር ማድረግ ሲፈልጉ አዘውትረው በንቁ! ይጠቀማሉ። ለምሳሌ ያህል ስለ ኦሎምፒክ ጨዋታዎች ትምህርት ሰጪ ርዕሶች የያዘው የመስከረም 8, 2000 እትም (እንግሊዝኛ) በጣም ጠቃሚ ነበር። በመሆኑም የተለያዩ የንቁ! እትሞችን በብዛት እንድትልኩልን ልጠይቃችሁ እወዳለሁ። ለወጣቶች ገንቢ የሆኑ ጽሑፎች ለማቅረብ የማደርገውን ጥረት እንደምትደግፉት አልጠራጠርም።”
እያንዳንዱ የንቁ! እትም መጽሔቱ የሚታተምበትን ምክንያት በገጽ 4 ላይ ይገልጻል። “ከሁሉም በላይ ይህ መጽሔት አሁን ያለውን ክፉና ዓመፀኛ ሥርዓት የሚተካ ሰላም የሰፈነበትና አስተማማኝ አዲስ ዓለም እንደሚመጣ ፈጣሪ በሰጠው ተስፋ ላይ ሰዎች ያላቸውን እምነት እንዲያሳድጉ ያደርጋል” ሲል ያብራራል።
የይሖዋ ምሥክሮች ይህንን ዓላማ ለማሳካት ታስበው የተዘጋጁ ብሮሹሮችንም ያቀርባሉ። ከነዚህም አንዱ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው? እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ? የሚለው ብሮሹር ነው። ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ አለዚያም ደግሞ በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው በመላክ ይህን ብሮሹር ማግኘት ይችላሉ።
□ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው? እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ? የተባለውን ብሮሹር ላኩልኝ።
□ መጽሐፍ ቅዱስ መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።