ትዳርን ለመታደግ የሚረዳ መጽሐፍ
በዩናይትድ ስቴትስ ሉዊሲያና የምትኖር ሌስሊ የተባለች አንዲት ሴት ባለፈው ዓመት ከቱላን ዩኒቨርሲቲ ተወካይ ስልክ ይደወልላታል። የደወለችላት ሴት ቱላን ከሌላ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በሉዊሲያና በሚኖሩ አዲስ ተጋቢዎች ላይ ጥናት እያካሄደ መሆኑን ትነግራታለች።
ሌስሊ በጥናቱ ለመካፈል ተስማማችና መጠይቅ ተላከላት። እርስዋም መጠይቁን ከሞላች በኋላ ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? ከተባለው መጽሐፍ ጋር ላከችው። እሷና ባለቤቷ የይሖዋ ምሥክሮች እንደሆኑና ለመጋባት በዝግጅት ላይ ሳሉ ይህንን መጽሐፍ አብረው እንዳጠኑት ገልጻ ጻፈች።
ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ከፕሮጀክቱ አስተባባሪ እንደሚከተለው የሚል ደብዳቤ ደረሳት:- “እንደ እናንተ ያሉ ጥንዶች ትዳርን ጠንካራና አስደሳች ለማድረግ ስለሚያስፈልጉት ነገሮች እንደሚያስተምሩን ተስፋ እናደርጋለን። የተለያየ አስተዳደግ ቢኖራችሁም እንኳን ብዙውን ጊዜ በዚህ ምክንያት በትዳር ውስጥ የሚፈጠረውን ችግር መፍታት መቻላችሁ ትኩረት የሚስብ ነው። የላክሽውን ዓይነት መጽሐፍ በመሳሰሉ ጽሑፎች በመጠቀም ለትዳራችሁ ቅድመ ዝግጅት ማድረጋችሁ ሊነሳ የሚችል ማንኛውንም አለመግባባት ለማስተካከል ያስችላችኋል። ደግሞም አንድ ትዳር በሃይማኖት ላይ የተመሠረተ መሆኑ ጠንካራ እንዲሆን ከሁሉ የላቀ አስተዋጽኦ ያበረክታል። ሁለታችሁም ጠንካራ እምነት ያላችሁና በአምላክ እርዳታ ላይ የምትመኩ በመሆናችሁ እድለኞች ናችሁ።”
“የላክሽልኝን መጽሐፍ ጠረጴዛዬ ላይ በግልጽ በሚታይ ቦታ አስቀምጬዋለሁ፤ ከአሁን በኋላ ተማሪዎቼ ስለ ትዳር ጥያቄ በሚያቀርቡልኝ ጊዜ ይህንን መጽሐፍ አሳያቸዋለሁ። ይህንን መጽሐፍ ከዚህ ቀደም አይቼው ባላውቅም በጣም ድንቅ መጽሐፍ ነው።”
እርስዎም ይህንን መጽሐፍ ጠቃሚ ሆኖ እንደሚያገኙት እናምናለን። የዚህን መጽሐፍ የግል ቅጂ ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ እባክዎ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ አለዚያ ደግሞ በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው ይላኩ። የሚያጋጥሙዎትን ችግሮች ለመፍታት ሊረዱ የሚችሉና ፈጣሪ መጀመሪያ ላይ አቅዶት በነበረው መሠረት የቤተሰብዎን ሕይወት አስደሳች ለማድረግ የሚያስችሉ ቀጥተኛ ሐሳቦችን ያገኛሉ።
□ ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ላኩልኝ።
□ መጽሐፍ ቅዱስ መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።