የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g02 8/8 ገጽ 32
  • “ጥሩ ጊዜ ላይ ደረሰኝ”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ጥሩ ጊዜ ላይ ደረሰኝ”
  • ንቁ!—2002
ንቁ!—2002
g02 8/8 ገጽ 32

“ጥሩ ጊዜ ላይ ደረሰኝ”

አባካሊኪ በምትባል ከተማ የሚኖር አንድ ሰው በናይጄርያ ለሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች ቅርንጫፍ ቢሮ በጻፈው ደብዳቤ ላይ ከላይ ያለውን ብሎ ነበር። ሰውየው በቅርብ ጊዜ ስለደረሰው የምትወዱት ሰው ሲሞት የተባለ ብሮሹር ሲናገር እንዲህ ብሏል:-

“ሰኔ 18, 2000 ውዷ ባለቤቴ ቶቺ ልጃችንን እንደወለደች ሞተችብኝ። ይህ ከሆነ ከአንድ ወር በላይ ቢያልፍም ድንጋጤው፣ የሚሰማኝ የመደንዘዝና የባዶነት እንዲሁም በሕይወቴ ካጋጠሙኝ ሁሉ የከፋውን ይህን አሳዛኝ ገጠመኝ ለማመን የመቸገር ስሜት ገና አልለቀቀኝም ነበር። ከዚያም በሐምሌ ወር ከይሖዋ ምሥክሮች አንዱ የምትወዱት ሰው ሲሞት የተሰኘውን ጽሑፋችሁን ሰጠኝ። ብሮሹሩ ልክ እንደ መድኃኒት ሆነልኝ። ብሮሹሩ ለሚያቀርበው ምክር ምስጋና ይግባውና በሱ እርዳታ ሕይወቴን ቀስ በቀስ እያስተካከልኩ ነው። ተስፋዬን አለምልሞልኛል፤ ሁሉም ነገር ጨልሞብኝ የነበረ ቢሆንም የብርሃን ጭላንጭል ፈንጥቆልኛል።”

ምናልባትም እርስዎም ሆኑ እርስዎ የሚያውቁት ሌላ ሰው ይህን ባለ 32 ገጽ ብሮሹር በማንበብ ማጽናኛ ማግኘት ትችሉ ይሆናል። ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ አለዚያም ደግሞ በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው በመላክ ይህን ብሮሹር ማግኘት ይችላሉ።

□ የምትወዱት ሰው ሲሞት የተባለውን ብሮሹር አንድ ቅጂ ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ